ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ በሀረሪ ክልል ስር የሰደደ ችግር ሆኗል፡፡

ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራ በሀረሪ ክልል ስር የሰደደ ችግር ሆኗል፡፡

የመሬት ወረራ እና ህገ ወጥ ግንባታ በክልሉ አሳሳቢ ችግር ከሆነ ግዜያት ያለፈው መሆኑን በሀረሪ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ሀላፊ አቶ አብዱልአዚዝ አብዱራህማን ገልፀዋል፡፡

 

በተጨማሪም ለውጡን ተከትለው የተከሰተ የህግ የበላይነት የማስከበር ክፍተት ህገ ወጥነት እንዲስፋፋ ማድረጉ ነው የተናገሩት ፡፡

 

አሁን ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ቢሆንም ከዚህ በፊት በህገ ወጥ መንገድ የተገነቡትን ለማፍረስ አስቸጋሪ መሆኑን ነው የገለፁት ፡፡

 

የቁጥጥር ስራ ለመስራት ህገ ወጥ ግንባታ እና የመሬት ወረራ የተካሄደባቸው  ስፍራ የሚሄዱ ሰራተኞች ማንነታቸውን ባልታወቁ ሰዎች የተለያየ ጉዳት ሲደርስባቸው  እንደነበር ነው አቶ አብዱልአዚዝ የተናገሩት ፡፡

 

ህግ አስከባሪ የሆኑ አካላት ከብልሹ አሰራር ወጥተው ለህግ የበላይነት እንዲሰሩ  ጠይቀዋል፡፡

 

ህገ ወጥ ግንባታና የመሬት ወረራዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ አንፃር የተለያዩ ስራዎች እየሰሩ እንደሆኑ ነው የተናገሩት ፡፡

 

የወረዳ አስተዳዳሪዎች እና የፖሊስ አባላት በቁርጠኝኘት በመስራት ይህን የህገ ወጥ ተግባራትን በጋራ ልንከላከል ይገባል ብለዋል፡፡

 

ህብረተሰቡም የህገ ወጥ መሬት ወረራ በሀገሪቱ ላይ የሚያደርሱትን ችግሮች በመረዳት ከመንግስት ጎን ሊቆም ይገባል ሲሉ  አቶ አብዱልአዚዝ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ ነሲም መሀመድ ኑር

23 7 13