ለሀረሪ ሕዝብ በሕገ መንግሰቱ የተሰጠው መብት ሊከበር ይገባል ሲሉ የአባድር ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

ለሀረሪ ሕዝብ በሕገ መንግሰቱ የተሰጠው መብት ሊከበር ይገባል ሲሉ የአባድር ወረዳ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

ከሐረሪ ክልል ውጭ ነዋሪ የሆኑ የሀረሪ ብሄረሰብ አባላት ባሉበት አካባቢ የሐረሪ ጉባኤ አባላትን መምረጥ እንዲችሉ በአባድር ወረዳ ነዋሪዎች ባካሄዱትውይይት ጠይቀዋል፡፡፡

የሐረሪ ብሔረሰብ እንደሌሎች አናሳ ብሄሮች በተለያዩ ግዜያት እንግልት እና ጫና ደርሶበት የኖረና ከመኖሪያ አካባቢውም በመሰደድ በሀገሪቷ በተለያዩ አካባቢዎችም ተበታትነው የሚኖሩ የሀረሪ ተወላጆች አሉ፡፡

 

በዚህም መሰረት በ1987 የኢትዮጲያ ሽግግር መንግስ ት ሲቋቋም በተለያዩ አካባቢዎች ተበታትነው የሚኖሩ ሀረሪዎች ባሉበት አካባቢ ሆነው ልዩ የመራጮች መዝገብ ተዘጋጅቶ በክልሉ የሀረሪ ጉባኤ ምክር ቤት አባላት እንዲመርጡ ተወስኖ ባለፉት 5 ምርጫዎች ይህ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

 

በዘንድሮው 6ተኛው ብሄራዊ ምርጫ ከሀረሪ ክልል ውጭ የሚኖሩ ሀረሪዎች መምረጥ እንዲችሉ ምርጫ ቦርድ ልዩ የመራጮች መዝገብ አላዘጋጀም፡፡

 

ምርጫ ቦርድ ሚያዝያ 1/2013 በማሕበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ ባደረገው ጽሁፍ ከሀረሪ ክልል ውጭ ያሉ ሀረሪዎች እንዲመርጡ መፍቀድና ማስደረግ የማይችል መሆኑን ገልጧል፡፡

 

በዚህም መሠረት አባድር መረዳ ነዋሪዎች ሀረሪዎች ከሀረሪ ክልል ውጭ የሚኖሩ ሀረሪዎች መብተቻው ሊከበር ይገባል ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡

 

የውይይት መድረኩን ሲመሩ የነበሩ አቶ ኻሊድ አብዲ የመድረኩን አላማ አስመልክተው እንዳሉት የምርጫ ሕግ ስላልተቀየረ የሀረሪ ሕዝብም ከዚህ በፊት በነበሩ ምርጫዎች ላይ ሲከበርለት የነበረ አሰራር ተግባራዊ እንዲሆን ለመጠየቅ ነው ብለዋል፡፡

 

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸውም ይህ የማንነት ጉዳይ ነው ስለዚህ ሁሉም ሀረሪዎች መብታቸው እንዲከበር በፖለቲካና በሌሎችም አመለካከት ሳይለያዩ በአንድነት ድምጻቸውን ሊያሰሙ ይገባል ብለዋል፡፡

 

በቀጣይም ከሀረሪ ክልል ውጭ ያሉ ሀረረዎችንም ባሳተፈ መልኩ ትልቅ የውይይት መድረክ ሊዘጋጅ እንደሚገባም ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

 

ሐምዛ ዩሱፍ

2 8 13