ለሁለት ቀናት የሚቆይ የቴክኖሎጂ ስራዎች ማሳያ ኢግዚቢሽን በክልሉ ፖሊ ቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተከፈተ፡፡

ለሁለት ቀናት የሚቆይ የቴክኖሎጂ ስራዎች ማሳያ ኢግዚቢሽን በክልሉ ፖሊ ቴክኒክና ሞያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ተከፈተ፡፡

     የሐረሪ ክልል ፖሊ ቴክኒክ እና ሞያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ በኮሌጁ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች የተሰሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች ማሳያ ለ2 ቀናት የሚቆይ ኢግዚቡሽን በትላንትናው እለት ተከፍቷል፡፡

 

 በኢግዚቢሽኑ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ዘከርያ አብዱላዚዝ የቴክኖሎጂ ኢግዚቢሽን ለረጅም ግዜት ሲያዘጋጁ መቆየታቸው ገልፀው በዘንድሮ መርሃ ግብርም ለህብረተሰቡ የተለያ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በአሰልጣኝ መምህራን እና በአሰልጣኝ ተማሪዎች ማካሄዳቸውን ገልፀዋል፡፡

 

ኮሌጁ በክልሉ ለሚገኙ ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም ቴክኖሎጂዎችን 100 በመቶ በመቅዳትና ናሙና በማዘጋጀት ተገቢ ፍተሻ ተደርጎ ለአብዚዎች በማስተላለፍ ኢንተርፕራይዞች ሀብት እንዲያፈሩ አስተዋፆ ማበርከታቸውን አቶ ዘከርያ ገልፀዋል፡፡

 

የሀረሪ ክልል ቴክኒክና ሞያ ትምህርት ስልጠና  ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃሚ መሀመድ በቴክኒክና ሞያ ተቋማት የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች በተግባር የተደገፉ አዋጪነታቸው ተረጋግጠው ለአብዢዎች ተላልፈው በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲደርሱ እንደሚሰራ ጠቅሰው በኮሌጁ የሚዘጋጁ ቴክኖሎጂዎች ወቅቱን የጠበቁና የገበያውን ፍላጎት ያማከሉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

 

ኮሌጁ በየወቅቱ የሚያደርጋቸውን የቴክኖሎጂ ስራዎች እና ሌሎች ተግባራት ኤጀንሲው ሲደግፍና ሲያበረታቱ መቆየቱን የጠቀሱት አቶ ጃሚ በቀጣይም በኮሌጁ ለሚከናወኑ ማንኛውም ተግባራት የኤጀንሲያቸው ድጋፍ እና እገዛ ከምንጊዜውም በላይ እንደማይለያቸው አረጋግጠዋል፡፡

 

የዕለቱ የክብር እንግዶች  የሐረሪ ክልል ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ደሊላ ዩሱፍ እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ የቴክኖሎጂ  ስራዎች ማስተዋወዊያ ኢግዚቢሽኑን በይፋ ከፍተዋል፡፡

 

በኢግዚቢሽኑ ላይ የተለያየ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውጤቶች ቀርበዋል፡፡

 

አነስተኛ መኪና፤የፕላስቲክ ማቅለጫ ማሽን፤የብረት ማጠፊያ ማሽን ፤የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማሽን እና በርበሬ መደለዣ ከቀረቡት የቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ጥቂቶች ናቸው ፡፡

 

ከ40 በላይ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ውጤቶች የቀረበበት ኢግዚቢሽኑ ለህዝብ ክፍት የሆነ ሲሆን ዛሬም ቀጥሎ እንደሚውል ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 ዘጋቢ ቤተልሄም ደሴ

8 8 13