ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ያነጋገርናቸው የባቢሌ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስኬት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ያነጋገርናቸው የባቢሌ ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የሐረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ ከባቢሌ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

በዚህ አመት የሚካሄደው ምርጫ በሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንደሚጠናቀቅ የባቢሌ ወረዳ ነዋሪዎች ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል፡፡

 

የፖለቲካ ፓርቲዎች የህዝብን ሰላም ከሚያደፈርስ አካሄድ እና ሀሳብ በመቆጠብ  የህዝብ ውሳኔን ለማክበር መዘጋጀት እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡

 

  አቶ ኡስማኤል ሸኮ የባቢሌ ወረዳ ቱላ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ ሲሆኑ ከዚህ በፊት ለአምስት ዙር የተካሄዱት ምርጫዎች የዲሞክራሲ ባህላቸው የተዳከመ እንደሆነ ተናግረው ይህ ደግሞ ሀገራችን ከዲሞክራሲ ባህል አኳያ ለከፍተኛ ችግር እንድትዳረግ እና ህዝብ በሀገር ላይ ያለውንም እምነት ያጠፋ እንዲሆን ማድረጉን ተናግረው  የአሁኑ ግን ወደ ዲሞክራሲ የሚያሸጋግረን መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

 

በሌላ በኩል የህዝብ ዘንድ ሆነ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዘንድ ያለው የዲሞክራሲ ባህል ደካማ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

 ለሀረሪ መገናኛ ብዙሀን ኤጀንሲ አስተያየታቸውን የሰጡ የባቢሌ ወረዳ ነዋሪዎች አንዳንድ አካላት ይህ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዳይካሄድ አጋጣሚውን የሐገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ ሊጠቀሙበት እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ህዝቡ  ይህን ተገንዝቦ ሰላሙን ማስጠበቅና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ራሱን ማዘጋጀት ይገባዋል ብለዋል፡፡

 

  ከዚህ በፊት የተካሄዱት ምርጫዎች ሰላም እንዲደፈርስ እና አለመረጋጋት እንዲፈጠር ያደረጉ  እንደነበር ገልፀው በፊታችን ግንቦት የሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫም ካለፉት ምርጫዎች ስህተቶቻችን በመማር በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ  ይገባል ብለዋል፡፡

 

እንዲሁም በማህበራዊ ሚዲያ የሚነዙ የተዛቡ የውሸት መረጃዎችን ነቅቶ በመለየት ከስህተት መቆጠብ ይገባል ብለዋል፡፡

 

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በግንቦት ወር እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

 

ዘጋቢ ምስክር አለማየሁ

20 7 13

Files