ሕይወታቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

ሕይወታቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ዜጎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በጉዳና ላይ የሚተዳደሩ ሴቶችና ሕጻናቶች የተለያዩ ጎጂ ድርጊቶች ጉዳት ሰለባ እንደሚሆኑ አያሻክም ፡፡

 

ስታንድ ፎር እንቴግሬትድ ዲቨሎፕመንት ድርጅት በጎዳና ላይ የሚተዳደሩ ዜጎች በተለይ ሴቶችና ሕጻናቶች በቤተሰብ ታቅፈው መኖር እንዲችሉ ለማድረግ ጎዳና ላይ የወደቁ ሴቶችን ከነ ልጆቻቸው አንስተው በማሕበራዊና በኢኮኖሚም ራሳቸውን እንዲችሉ ለማስቻል የሕይወት ክህሎት ስልጠና እና ስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የተለያዩ ትምህርቶችን በመስጠት አስተሳሰባቸውን እንዲቀይሩ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

 

ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በስሩም 31 እናቶችና 28 ህጻናት ያቀፈ ነው፡፡

 

ይህ ድርጅት በዚህ ብቻ ሳያበቃ እነኚህ ከጎዳና ላያ ያነሳቸውን ዜጎችን ለ4 ወር ገደማ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ከወሰዱ በኃላ እራሳቸውን የሚችሉበት ስራ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልጻል፡፡

 

ድሮ ጎዳና ላይ ሕይወታቸው ይመሩ የነበሩና አሁን በድርጅቱ ውስጥ ታቅፈው ሕይወታቸውን ጻእየመሩ ካገኘናቸው ሴቶች መካከል አንዳንድ ያነጋርናቸው ሴቶች እንደተገለፁት ጎዳና ላይ በነበሩበት ጊዜ ለብዙ ችግር ሰለባ እንደሆኑ ገልጸው አሁን ግን በጥሩ ሁኔታ እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን አመልክተው  ከዚህ ጎን ለጎንም የተለያዩ ትምህርቶችና የሕይወት ክህሎት ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በድርጅቱ ውስጥ የጤና አግልግሎት ባለሙያ የሆነችው ወ/ሪት ሰአዳ አብራሂም በበኩላቸው ድርጅቱ የሚሰጠውን አገልግሎት በዋናነት ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናትና በጎዳና ላይ ለሚተዳደሩ ሴቶች ለሱስ ሰለባ የሆኑትንም ከሱስ ተላቀው በማሕራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ራሳቸውን ችለው ጥሩ ሕይወት እንዲኖራቸው ለማስቻል ድርጅቱ በዋናነት እየሰራ መሆኑን ገልጻለች፡፡

 

በተጨማሪም ድርጅቱ ውስጥ ለ4 ወር ገደማ እንክብካቤ ከተደረገላቸው በኃላ በነበሩበት አስተሳሰብ ከተላቀቁ በኃላ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ወስደው ራሳቸውን እንዲችሉ የተለያዩ የስራ መስክ ላይ እንደሚሰማሩ ነው የገለጸችው፡፡

 

ድርጅቱ 56 ወንዶች እና 27 እናቶች ከ15 ልጆቻቸው ጋራ ተመርቀው ራሳቸውን ችለው ሕይወታቸውን እየመሩ እንደሚገኙ መሆኑንም ገልጻ በተሰማሩት ሥራ መስክ ላይም ውጤታማ መሆናቸውንና ያሉበት ደረጃ የሚከታተል አካል እንዳለ ገልጻለች፡፡

 

በጎዳና ላይ የሚተዳደሩ ዜጎችን ለመቀነስ ድርጅቱ አቅዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሒዳያ ፉአድ

4 8 13