ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን የመራጮች ምዝገባ ያካሄዱ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን የመራጮች ምዝገባ ያካሄዱ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በሀረሪ ክልል  ከ200 በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን መራጮችም ለምርጫ የሚያስፈልጋቸውን ካርድ መውሰድ መጀመራቸውን ከሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ቆይታ ያደረጉ የምርጫ ምዝገባ ያካሄዱ ዜጎች ተናጋረዋል፡፡

 

በዲሞክራሲዊ መብታቸው ጠጠቅመው የበጀኛል ያጠቅመኛል ያሉትን የፖለቲካ ፓርቲ እና እጩዎችን ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

 

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ ፣ ፍትሃዊ ፣ ሰላማዊና በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ስኬታማ ምርጫ ፣ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

 

የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ሌሎች የክልሉ ነዋሪዎች በቀሩት ቀናቶች የምርጫ ካርድ በመወሰድ ለምርጫው ዝግጁ መሆን እንዳለባቸውም ነው  ተመዝጋቢ መራጮች የተናገሩት

 

ለስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 16 እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ እንዲሚካሄድ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መርአ ግብር ያመለክታል፡፡

 

ዘጋቢ ሄኖክ ግርማ

29  7 13