ቅድመ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የሀረሪ ቴሌቪዥን በሳተላይት ተሰደራሽ መሆን ሲጀምር የክልሉን ባህልና እሴት ይበልጥ ለማስተዋወቅ እድል ይፈጥራል ሲሉ ምሁራን ገለፁ፡፡

ቅድመ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የሀረሪ ቴሌቪዥን በሳተላይት ተሰደራሽ መሆን ሲጀምር የክልሉን ባህልና እሴት ይበልጥ ለማስተዋወቅ እድል ይፈጥራል ሲሉ ምሁራን ገለፁ፡፡

ላለፉት አመታት በሬዲዮ ኤፍ ኤም ና በአንቴና የቴሌቪዥን ስርጭት ተወስኖ የነበረው የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ የአድማጭ ተመልካቹን ፍላጎት ለማርካት አሁን ላይ ዘመኑ የወለዳቸው የዘርፉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከወትሮ በተለየ ጥራትና ይዘት ተወዳዳሪ ለመሆን የተለያዩ ሥራዎችን እየከወነ ይገኛል፡፡

 

የሬዲዮ ስርጭቱን ለማዘመን ሥራ ላይ ያዋላቸውን ቴክኖሎዎችን ጨምሮ በቅርቡ ለሚጀምረው የሳተላይት ቴሌቪዥን ስርጭት የተለያዩ የትግበራ ምዕራፎችን አልፏል፡፡

 

ሚዲያው የሳተላይት ስርጭቱን ሲጀምር ለሌላ አድማጭ ተመልካች ፈጣን መረጃን ከማድረስ ባለፈ ለአካባቢው ማሕበረሰብ ከቅርበት አንጻር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ከሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ተግባቦት ትምህርት ክፍል አስተባባሪው መምህር ደህናሰው ሽመልስ ተናግረዋል፡፡

 

ከዚህ ባለፈም ይላሉ መምህሩ የምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል በተለይ ደግሞ የረጅም አመታት ታሪክ ባለቤት የሆነችው ሐረር  በእልፍ እሴት፣ ባህልና ወግ የተቃኘች በመሆኗ ለተቀረው የሀገሪቱ ክፍል አድማጭ ተመልካች አልፎ ለአለም አቀፉ ማሕበረሰብ ይህን ቱባ ባህል ለማስተዋወቅ ብሎም በእያንዳንዱ ልብ ውስጥ አይረሴ ለማድረግ  የሚዲያው ወደ ሳተላይት ስርጭት መወጣት ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ይህም የሚሆነው ይላሉ መምህር ደህናሰው አቀራረብና ይዘቱ በሚገባ የተዋቀረ እንደሆነ ነው በማለት ያነሳሉ፡፡

 

መገናኛ ብዙኃኑ ወደ ሳተለይት ስርጭት ማደጉ ለተደራሲን አማራጭ የመረጃና የመዝናኛ ቻናል እንዲሆን ያስችለዋል የሚሉት መምህሩ ከሌሎች አቻ መገናኛ ብዙኃን ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን የይዘትና የአቀራረብ ጉዳዮችን በጥልቀት ማየት እንዳለበት ምክረ ሃሣባቸውን ሰጥተዋል፡፡

 

የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ በቅርብ ቀናት ውስጥ ስርጭቱን ይጀምራል፡፡

 

ዘጋቢ ወንድሙ አዱኛ

30 7 13