በሀረሪ ክልል ለሚገኙ 3 ትምህርት ቤቶች የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ድጋፍ ተደረገ፡፡

በሀረሪ ክልል ለሚገኙ 3 ትምህርት ቤቶች የውሃ መሳቢያ ፓምፕ ድጋፍ ተደረገ፡፡

በአዲስ አበባና በሀረሪ ክልል እየሰራ እንደሚገኘም የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ተናግረዋል፡፡

ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል የሐረር ከፍተኛ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር አቶ አቡሽ ስለሺ እንደተናሩት በትምህርት ቤቱ ከፍተኛ የውሃ አቅርቦት ችግር እንደነበር ተናግረው ወርልድ ቪዥን አሁን ያደገላቸው የውሃ መሳቢ ፓምፕ ድጋፍ ችግሩን እንደሚቀርፍና ኮሮናን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የየሺመቤት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን ወይዘሮ በላይነሽ ለገሰ የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በድርጅቱ በኩል ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተደረገው የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብዓት የመማር ማስተማሩን ሂደት እያገዘው እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የሐረር ሀማሬሳ ኒኮላስ በም 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር የሺ ከበደ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ኮሮናን በጋራ እንከላከል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ውሀና ፍሳሽ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ሀይል ሰብሳቢ አቶ ወሊድ አብዲ በድጋፉ ወቅት  እንደተናገሩት ትምህርት ቤቶች ውሃ እንዲያገኙ ጥረት መደረጉን ተናግረው  ጤናማ የትምህርት አሰጣጥ እንዲኖር የቅሃ አቅርቦት ላይ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

የወርልድ ቪዥን ኢትጵያ በሀረርጌ ክላስተር ማስተባበሪያ ላይ የኢመርጀንሲ ዋሽ ኦፊሰር  እንደተናሩት ይህን ፕሮጀክቱን በፋይናንስ የደገፈው የፊንላንድ ፕሮጀክት መሆኑ ተናግረው በአዲስ አበባና በሀረሪ ክልል በ400 ሺ ዶላር በጀት እየሰራ ያ ፕሮጀክት መሆኑነ ገልጸዋል፡፡

ኦፊሰሩ አክለውም አሁን የተደረጉት የውሃ መሳቢያ ፓፕፖቹ ኮሮናን ከመከላከል አንፃር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖራቸው ተናግረው ከዚህ ቀደምም ለተመረጡ አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች የሳሙና እና  የሳኒታዘር የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ አሚር ኡስማን 
 26 5 13