የሀረሪ ክልል የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ጽ/ቤት ባለፉት 3 አመታት ለ7708 ወጣቶች በቋሚና በጊዜያዊነት የስራ እድል በመፍጠር ወጣቶችን ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል ፡፡

በክልሉ በ1998 ዓ/ም የወጣት ፓኬጁ ከፀደቀ ጊዜ ጀምሮ ወጣቶች በኢኮኖሚ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ ተጠቃሚና ተሳታፊ መሆን ችለዋል ፡፡ የተለያዩ የቴክኒክና ሞያ  ስልጠና በመስጠት ከ1998 ጀምሮ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ማህበራት ብዛት 201 ናቸው ፡፡ ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2007 ዓ/ም ድረስ ለ7708 ወጣቶች በቋሚነትና በጊዜያዊነት የስራ እድል መፍጠር መቻሉን የገለፁት የክልሉ የሴቶችና ወጣቶች ተሳታፊና ተጠቃሚ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት  አቶ አብዱረህማን ዩሱፍ ናቸው ፡፡

በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በሀረሪ ክልል በገጠርም ሆነ በከተማ ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባትና ወጣቶች ራሳቸውን ከሱስ እንዲያርቁ ለማድረግ ባሉት የወጣት ማዕከላት ተጠቃሚ በሚሆኑበት መንገድ ጥሩና ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን  አቶ አብዱረህማን አክለው ገልፀዋል ፡፡

በተጨማሪም በመጀመሪያው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን ያልተሰሩ ስራዎችን በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን  ለመስራት ማቀዳቸውን ጠቁመዋል ፡፡

ዘጋቢ ኤልሳቤት ቤተ

NO COMMENTS

LEAVE A REPLY