በሀረሪ ክልል ነገ ለሚጀመረው የተፋሰስ ልማት ስራ መዘጋጀታቸዉን አርሶ አደሮቹ ገለፁ፡፡

0
400

የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የእርከን ስራ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በተፋሰስ ልማት ዘመቻ የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በሀረሪ ክልል የሚገኙ አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡

ነገ ቅዳሜ ለሚጀመረው 6ተኛ ዙር የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የእርከን ስራ ዝግጁ መሆናቸውን አርሶ አደሮቹ ገልጸዋል፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የእርከን ስራ ዘመቻ በሀገር አቀፍ ደረጃ መስራት ከተጀመረ ከተሰሩት የተለያዩ የልማት ስራዎች ከፍተኛ ጥቅም ማግኘቱንና ህብረተሰቡም ተጠቃሚ መሆኑን ተገለፀ፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የእርከን ስራ ዘመቻ በየአመቱ በጥር ወር የሚደረግ ሲሆን በሐረሪ ክልልም የፊታችን ቅዳሜ ለመካሄድ ዝግጅቱ መጠናቀቁ ተገልፃል፡፡

የሀረሪ ክልል አርሶ አደሮችም ከዚ በፊት ከተሰሩት ስራ ከፍተኛ ጥቅም ያገኙ መሆኑ በመግለፅ ለወደፊትም በተጠናከረ ሁኔታ ለመስራት ዝግጁ መሆቸውን ተናግረዋል፡፡

በመቀጠልም አርሶ አደሮቹ የልማቱ ስራ (ዘመቻው) ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን በማወቅ ሌት ተቀን ሳይሉ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

አርሶ አደሮቹ ባስተላለፉት መልዕክት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘመቻው ለመላው የክልሉ ህብረተሰብ ጠቃሚ መሆኑ ታምኖበት ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜት  ዘመቻው ላይ መሳተፍ እዳለበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የዘንድሮው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ዘመቻም የእርከን ስራ ዘመቻ ለማከናወን 25 ተራራማ ስፍራዎች በመለየት ዘመቻውን ለመጀመር ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁት ለዝግጅቱት የተደራጀው የልማት ሰራዊት ነው፡፡

ዘጋቢ ዲኔ መሀመድ

NO COMMENTS