በሀረሪ ክልል የኮቪድ 19 ክትባት ለመስጠት ለማስጀመሪያ ከተዘጋጀው 150 ክትባቶች 143 መሰጠቱን የሐረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በሀረሪ ክልል የኮቪድ 19 ክትባት ለመስጠት ለማስጀመሪያ ከተዘጋጀው 150 ክትባቶች 143 መሰጠቱን የሐረሪ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ፡፡

በሀገሪቷ ከመጋቢት 4 ጀምሮ የኮቪድ 19 ክትባት እንዲሰጥ መደረጉ ይታወሳል፡፡

 

ነገር ግን በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች የክትባቱ አስጊነትና የጎንዮሽ በሽታዎችን እንዳለው በአለም ላይ ትልቅ ውዥንብሮችን ፈጥሯል፡፡

 

ሆኖም በኢትጵያ ላይ ክትባቱ ቢጀመርም ከህብረተሰቡ ዘንድ የግንዛቤ እጥረት ችግር በመኖሩ በታቀደው ደረጃ እንዳይሄድ አድርጎታል፡፡

 

 በዚሀም በሀረሪ ክልል ህብረተሰቡ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ትቷል ፡፡

 

በተጨማሪም ክትባቱን ለመወውሰድ የተሰራጩት ማረጋገጫ የሌለው መረጃም ተወዛግቦ ስለ ክትባቱ ያላቸው አመለካከት የተዛባ ሆኗል፡፡

 

ይህን በተመለከተም የሐረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ከሀረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ የእናቶችና ህጻናት እንዲሁም የክትባት አስተባባሪ አቶ ተካልኝ ሞርካ ጋር ቆታውን አድርጓል፡፡

 

በቆይታችንም አቶ ተካልኝ እንዳሉት ህብረተሰቡ የኮቪድ 19ኝን  ለመከላከል መተግበር  ያለባቸውን የጥንቃቄ መርህ ባለመከተላቸው  ዋጋ እያስከፈለን ነው ብለዋል፡፡

 

ባሁኑ ወቅት ክትባቱን  ለማስጀመር ከተዘጋጀው 150 ክትባት 143 መስጠቱን ገልፀው በቀጣይ በሰፊው ለመስጠትም እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

 

ቢሮው አሁን ያለውን የህብረተሰብ የመዘናጋት ችግርን ለማጥፋትና በክትባቱ ዙርያ ያለውን መሠረተቢስ የሆኑ አወዛጋቢ መረጃዎችና ግንዛቤዎችን ለማስወገድ ለተለያየ ተቋማት፤የማህረሰብ ክፍሎችና ለሲቪል ማህበራት የተዘጋጁ የቅስቀሳ መድረኮችንና የስልጠና ፕሮግራሞች እንዳሉም ተናግረዋል፡፡

 

በዚህም ከተለያዩ የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት ለተወጣጡ ጤና ባለሞያዎች  በክትባት ዙርያ ግንዛቤና ክትባቱን አሰጣ ዙርያ ስልጠና ተሰጥቶ ተደራሽነቱን ለማስፋት ሰፊ ስራ በመስራት ላይ እንዳሉም አቶ ተካልኝ ጠቁመዋል፡፡

 

ህብረተሰቡ ክትባቱን ወስዶ የጥንቃቄ መመሪያውን ግን ካልተከተለ ግን  የክትባቱ መውሰድ ዋጋ አይኖረውም ያሉት አቶ ተካልኝ ሰዎች ክትባቱን ሲወስዱ ሰውነታው ቢቆጣም  ሌሎች ክትባቶችም ላይ የሚታዩ ተፅኖ አይነት ስለሆነ በስጋት ሊመለከተው አይገባም ብለዋል፡፡

 

ህብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ስለክትባቱ በቂ መረጃ ለማግኘት ወደ ጤና ባለሞያ መሄድ እንዳለበትም ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ ኢሊያስ መሀመድ

21 7 13