በሐረሪ ክልል የመንግስት በጀት የሚጠቀሙ ተቋማተ የውስጥ ኦዲት ምክክር ተካሄደ፡፡

በሐረሪ ክልል የመንግስት በጀት የሚጠቀሙ ተቋማተ የውስጥ ኦዲት ምክክር ተካሄደ፡፡

የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት በመንግስት በጀት የሚጠቀሙ ተቋማት የውስጥ ኦዲት የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

 

የውይይት መድረኩን የሀረሪ ክልል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አዲስዓለም በዛብህ እና የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር መርተውታል፡፡

 

መድረኩን  በንግግር የከፈቱት አፈጉባኤዋ የመንግስት በጀትን በአግባቡ የማይጠቀሙ እና በወቅቱ ሪፖርት በማያቀርቡ ተቋማት እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ እና የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ ተቋማን ማበረታታት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

 

በውይይቱ የውስጥ ኦዲት ግኝቶች ፁሁፉን በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ የውስጥ ኦዲት ክትትል እና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በሆኑት በአቶ ቦጋለ ለማ ቀርቧል፡፡

 

በውስጥ ኦዲት ግኝቶች ላይ የተሰሩ ስራዎች እና የነበሩ ክፍተቶችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

 

  በዚህም መሰረት የመንግስት በጀትን የንብረት አዋጅ መመሪያን ተግባራዊ አለማድረግ፤ ያልታወቀ የውስጥ ገቢ ገንዘብ ወጪ ማድረግ፤የወጪ ማስረጃ በቤት ውስጥ ማስገባት እና ያለፈው ኦዲት ሪፖርት ለኦዲት እቅድ መሰረት ቢሆንም ከዚህ አለመነሳት ችግር መኖርን በኢዲት ግኝት ላይ ያሉ ክፍተቶችን መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

 

ከ8 መስሪያ ቤቶች በጉድለት 486 ሺ 319 ብር 30 ሳንቲም መገኘቱን 182 ሺ 748 ብር 67 ሳንቲም ደግሞ ተመላሽ ማድረጋቸውንም በሪፖርቱ ላይ ገልፀዋል፡፡

 

እንዲሁም 3 ሚሊየን በክትትል ወደ ትሪዠሪ  ገቢ እንዲሆን ማድረጉንም በፁሁፍ ላይ አቅርበዋል፡፡

 

ተቋማት በየግዜው ለሚሰጠው ስልጠና እራስን አለማዘጋጀት ከአቅም በታች የውስጥ ኦዲት እቅድ ማቀድ እና ስራን  ማከናወን   ክፍተቶች መኖራቸው በሪፖርቱ ጠቁመዋል፡፡

 

በተጨማሪም በ2012 የኦዲት ሪፖርት አብዛኛው ተቋማት ሪፖርት ያቀረቡ ቢሆንም  የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት፤ጠቅላይ አቃቤ ህግ፤ኢንተርፕራይዞች ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ፤ ባህል ቅርስ እና ቱሪዝም ቢሮ ፤ግብርና ልማት ቢሮ ፤ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ፤ስፖርት ኮሚሽን ፤ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ጀኔላ፤ሀኪም፤ድሬ ጠያራ፤ሶፊ እና ኤረር ወረዳዎች ሪፖርት አለማቅረባቸውን አቶ ቦጋለ በፁሁፍ አመላክተዋል፡፡

 

ተቋማት የስራ ሀላፊዎች በውይይት መድረኩ በቀረቡ የግኝት ሪፖርት እና በተቋሞቻቸው ላይ በተነሱ ሀሳቦች ላይ አስተያየት እና ማብራሪያ  ሰጥተዋል፡፡

 

የሐረሪ ክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ሀላፊ ዶክተር አብዱላሂ አህመድ ወዚር በክልሉ ያሉ መመሪያዎች ማስፈፀም ላይ የፋይናንስ ቢሮ እና የሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ሊሰሩበት እንደሚገባ በኦዲት ላይ የሁሉም ተቋማት አመራሮች ሰራተኞችን ለማብቃት ስልጠና አዘጋጅተው የመስጠት ሀላፊነት እንዳለባቸውም በምክክር መድረኩ ላይ አንስተዋል፡፡

 

የተቋማት አመራሮች ለኦዲት ስራ ትኩረት በመስጠት እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባም ዶክተር አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

 

  የሐረሪ ክልል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ አብዱልባሲጥ አቡበከር 80 በመቶ የመንግስት በጀት የሚገኘው በድጎማ በመሆኑ ያንን የድጎማ ገንዘብ ለማግኘት የሚቻለው ሪፖርት በአግባቡ እና በወቅቱ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ በመሆኑ ሪፖርት በወቅት ለማቅረብ አመራሩ እንደመደበኛ ስራው በመቁጠር ሊሰሩ እንደሚገባ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ አስገንዝበዋል፡፡

 

በቀጣይም ከተቋማት ጋር ቅንጅታዎ አሰራር ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

 

በመጨረሻም የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አዲስዓለም በዛብህ ህገ መንግስቱን የተንተራሰ ደንብ እና መመሪያ እንደ ክልል ሊዘጋጅ እንደሚገባ ተናግረው ፋይናንስ ቢሮ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ኦዲት ቢሮ በቅንጅት የመመሪያ ዝግጅት በማድረግ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

የየተቋማቱ የኦዲት ባለሞያው የእውቀት ክፍተቶች መኖራቸውን ከሪፖርቱ መገንዘባቸው የጠቀሱት ወይዘሮ አዲስ ዓለም በዚህ ላይ ተቋማት ራሳቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 

ዘጋቢ ቤተልሄም ደሴ

7 8 13