በሕገ መንግስት የተረጋገጠውን የአናሳ ብሔረሰብ መብትን ተከትከሎ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን ልዩ የመራጮች ምዝገባ አለካሄዱ ከፍተኛ ቅሬታ የፈጠረባቸው መሆኑን የሀረሪ ብሄረሰብ ወጣቶች ገለፁ፡፡

በሕገ መንግስት የተረጋገጠውን የአናሳ ብሔረሰብ መብትን ተከትከሎ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን ልዩ የመራጮች ምዝገባ  አለካሄዱ ከፍተኛ ቅሬታ የፈጠረባቸው መሆኑን የሀረሪ ብሄረሰብ ወጣቶች ገለፁ፡፡

ወጣቶቹ በኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውሳኔና በክልሉ ሕገ መንግስት የተሰጣቸውን የአናሳ ብሔረሰብ መብትን ምረጫ ቦርድ እንዲያከብርላቸው ጠይቀዋል፡፡

 

በ1987 በነበረው የሽግግር መንግስት ወቅት ለአናሳ ቤሔረሰብ በተለይም ለሀረሪ ሕዝብ በልዩ የምርጫ መዝገብ በልዩ የምርጫ ካርድ ሁሉም የብሔረሰብ ተወላጅና በተለያዩ በሀገሪቱ ክፍል ተብትነው የሚገኙ የብሄረሰብ ተወላጆች ባሉበት ቦታ ሆነው ለሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤ ምክር ቤት ለክልሉ ያስተዳድራል የሚሉትን የሚመርጡበት በኢ.ፊ.ድ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ ተቀምጧል፡፡

 

በዚህ መሠረት በሀገሪቱ በነበሩ 5 ምርጫዎች በተሰጣቸው ሕገ መንግስታዊ መብት ሁሉም የብሔረሰብ ተወላጆች ባሉበት ሆነው ለክልሉ የሀረሪ ጉባኤ ድምጻቸውን ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡

 

ቢሆንም በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሀረሪ ብሔራዊ ጉባኤን የሚያሳትፍ መዝገብም ሆነ ልዩ የምርጫ ካርድ አለመዘጋጀቱን በክልሉም ሆነ ከዚህ ውጪ የሚገኙ ሀረሪዎችን  ብሔረሰቡን እያስቆጣ ይገኛል፡፡

 

የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው የሀረሪ  ወጣቶችም በሕገ መንግስቱ የተደነገገውን መብት ምርጫ ቦርድ ሊያስከብርልንና እና ሕገ መንግስቱን ሊያከብር ይገባል ብለዋል፡፡

 

ወጣት ነጂብ አብዱልአዚዝ ይህንኑ ሀሳብ ይጋራል፡፡

 

ከክልሉ ይህንን በተመለከተ እና ሕገ መንግስቱ የሰጠውን የአናሳ ብሄረሰብ መብትን ምርጫ ቦርድ ሳይሸራርፍ ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል ያለው ደግሞ ወጣት አሚር ረመዳን ነው፡፡

 

የሁለቱም ወጣቶች ሀሳብ የምትጋራው ወ/ሮ ኒኢሙት አብዲ የሀረሪ ጉባኤ የመብት ጥያቄ በአፋጣኝ መልስ ሊሰጥበት የሚገባ ጉዳይ ነው ስትል ተናግራለች፡፡

 

ወጣቶቹ በቀረበው የመብትና ሕገ መንግስት ጥያቄ ሁሉም የብሔረሰብ ተወላጆች በአንድነት ድምጻችንን ልናሰማ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

የሀረሪ ጉባኤ በተመለከተ ትናንትና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው ምላሽ ከክልሉ ውጭ ያሉ የብሄረሰብ ተወላጆች ለምክር ቤቱ ምርጫ ድምጽ መስጠት እንደማይችሉ ገልቷል፡፡

ሂዳያ ፉአድ

2 8 13