በቀርሳ ወረዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ለዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፈ ተካሄደ፡፡

በቀርሳ ወረዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ለዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፈ ተካሄደ፡፡

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቀርሳ ወረዳ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፈ ተካሂዷል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ ላይ በሀገር ግንባታ ላይ ኦሮሞ ህዝብ ያልተሳተፈበት አጋጣሚ የለም ሲሉ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን  የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ  አቶ መሀመድ ኡስማን ተናግረዋል ፡፡

ለሀገሪቱ ሰላም እና ልማት እንቅፋት የሚሆኑ አካላትን ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመሆን እንዲታገል የጠየቁት አቶ መሀመድ መንግስትም በእነኚህ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ ገልፀዋል፡፡ 

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የቀርሳ ወረዳ ነዋሪዎች በተለያዩ የባህል አልባሳቶች በማሸብረቅ ባህላዊ ጭፈራዎችን በማሳየት ለዶክተር አብይ ያላቸውን ፍቅርና ድጋፍ አሳይተዋል፡፡

በድጋፍ ሰልፉ የቀርሳ ወረዳ ወጣቶች የስፖርት ትርኢት በማሳየት ዝግጅቱን አድምቀውታል፡፡

የወረዳው ነዋሪዎች ህብረ ብሄራዊነትን በማጎልበት የአሃዳዊ ስርዓትን ለመጨረሻ ግዜ ለማስወገድ እና የአቃፊነት  ተምሳሌት የሆነውን የኦሮሞ ገዳ ስርዓትን ለማሳደግ እንተጋለን ብለዋል፡፡

ዶክተር አብይ አንድነት እና የልማት መሀንዲስ  መሆኑን በተግባር ያሳየ ጀግናችን ነው ለዚህም ክብር እና ምስጋና ያስፈልገዋል በማለት የቀርሳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ናስር አብዲ ተናግረዋል፡፡

የቀርሳ ወረዳ ነዋሪዎች  ከየአካባቢው  ተውታጥተው ለዶክር አብይ ያላቸውን ፍቅር እና ክብር አሳይተዋል፡፡

ዘጋቢ ፡ ጁንዲ ጀማል
26 05 2013