በባህላዊና ሀይማኖታዊ ቱፊቶች ዙሪያ ስልጠና የወሰዱ 42 ጎልማሶች ተመረቁ፡፡

በባህላዊና ሀይማኖታዊ ቱፊቶች ዙሪያ ስልጠና የወሰዱ 42 ጎልማሶች ተመረቁ፡፡

የሀረሪ ክልል ባህል ቅርጽና ቱሪዝም ቢሮ የሀረርን ታሪካዊ ቅርሶች ለማስጠበቅና ለትውልድ ለማሸጋገር እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

 

ቢሮው ለ34 ቀናት ሲያሰለጥናቸው የነበረውን 42 ስልጣኞች አስመረቀ፡፡

 

የሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የሀረርን ታሪካዊ ቅርሶች ለማስጠበቅና የባህሉ ባለቤት ያሉትን እሴቶች  እንዲያውቅ ለማስቻል ቢሮው ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን የቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ አዩብ አብዱላሂ ገልጸዋል፡፡

 

ሥልጠናው ለ42 ሰልጣኞች ሲሰጥ መቆየቱን የገለፁት ምትል ቢሮ ሓላፊው በስልጠናው ባህላዊና ሐይማኖታዊ ቱፉቶች መዳሰሳቸውን ጠቁመዋል፡፡

 

ቢሮው የሸዋል ኢድን በዩኒስኮ  የአልም ቅርስነት ለማስመዝገብ በነቂስ እየሰራ መሆኑንም አቶ አዩብ አክለው ገልጸዋል፡፡

 

ስልጠናው ለ34 ቀናት ሲሰጥ መቆየቱን የገለፁት በሀረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዳሬክተሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር አብዱረህማን ሰልጣኞች በአፎቻና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ መሆኑን ጠቁመው አላማው የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ለትውልድ ማስተላለፍ መሆኑን ገልጸዋል

 

ለተተኪው ትውልድ የሀረሪን ባህልና ታሪካዊ ቅርሶቹን ለማስተላለፍ ዘርፈ ብዙ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን አቶ እስክንድር ተናግረዋል፡፡

 

በምረቃ ስነ ስርዓቱ የቢሮው አመራሮችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

 

አለም ገመቹ

30 7 13