በአሚር ኑር ወረዳ የጤና መድህን በተሻለ ደረጃ አፈፃፀም እያሳየ መሆኑ ተናገረ፡፡ በጤና መድህን ዙርያ የህብረተሰቡ ግንዛቤም ከበፊቱ የተሻለ መሆኑ ተገልፃል;፡

በአሚር ኑር ወረዳ የጤና መድህን በተሻለ ደረጃ አፈፃፀም እያሳየ መሆኑ ተናገረ፡፡ በጤና መድህን ዙርያ የህብረተሰቡ ግንዛቤም ከበፊቱ የተሻለ መሆኑ ተገልፃል;፡

የጤና መድህን አገልግሎት መንግስት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህረተሰብ ክፍል አንድ ግዜ በሚፈፀም አነስተኛ ክፍያ መላው ቤተሰብ ህክምና እንዳገኙበት የተቀየሰ  አሰራር ነው ፡፡

 

በአሚር ኑር ወረዳው የጤና መድህን አስተባባሪ አቶ መሀመድ አብደላ በክልሉ የጤና መድህን ከተጀመረ አመታት ቢያስቆጥርም እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ የህብረተሰቡ ግንዛቤ አናሳ በመሆኑ በስፋት ሲጠቀሙ አይስተዋልም ነበር ብለዋል፡፡

 

ከቅርብ ግዜ ወዲህ መንግስት ትኩረት ሰጥቶበት በጤና መድህን ዙርያ ግንዛቤን ለማስፋት በመሰራቱ  እና ህብረተሰቡም ቀደም ሲል የጤና መድህን አባል የሆኑ አካላት ያገኙትን ጥቅም በተግባር ባዩ ግዜ በርካታ ዜጎች ወደ አባልነት እየመጡ ነው ብለዋል፡፡

 

ባለሙያው በማከልም አንድ  ሰው የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ካርድ ለማውጣት እና ለምርመራ ብቻ እንኳን የህክምናውን ሳይጨምር ከ500 ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል ነገር ግን የጤና መድህን ተጠቃሚ ከሆኑ በአመት 500 ብር በመክፈል ሙሉ ቤተሰብ አመቱን ሙሉ ሊታከም ይችላል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

 

ይህን በመገንዘብ ሌሎችም አባል  እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

በወረዳው የጤና መድህን አባል የሖኑት ወይዘሮ ኒሙት አብዲ የጤና መድህን አባል ከመሆናቸው በፊት ሲታመሙ ለመታከም ከፍተኛ ወጪ ያወጡ እንደነበር ተናግረው  የጤና መድህን አባል ከሆኑ በኋላ የአባልነት ካርዱን በመያዝ ብቻ በፈለጉት የመንግስት ጤና ተቋም የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ነው የገለፁት ፡፡

 

በአሚር ኑር ወረዳ የጤና መድህን ሽፋን ከአካባቢው ነዋሪ አንፃር 50 በመቶ ላይ ይገኛል፡፡

 

ዘጋቢ ሀምዛ ዩሱፍ

11 8 13