በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከወሰን ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመግባባት ለተፈናቀሉ  ዜጎች በሐረሪ ክልል  እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ ቀጥሏል፡

0
437

    በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከወሰን ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመግባባት ለተፈናቀሉ  ዜጎች በሐረሪ ክልል  እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ ቀጥሏል፡

  በክልሉ የሚገኙ ነጋዴ ማሀበረሰቦችም ለተፈናቃዮቹ  የምሳ ግብዣ  በዛሬው እለት አዘጋጅተዋል፡፡

4.01.2010

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከወሰን ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመግባባት ለተፈናቀሉ ከ1200 በላይ ዜጎች በሐረሪ ክልል ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከወሰን ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመግባባት ለተፈናቀሉ ከ1200 በላይ የሚሆኑ የሁለቱ ክልል ነዋሪዎች በሐረሪ ክልል ጀኔላ ወረዳ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አብዲሊማይ ገልጸዋል፡፡

የወረዳው ህብረተሰብም ለተፈናቃዮቹ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ከማድረግ አንጻር አበረታች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም አስተዳዳሪው ጠቁመዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ንግድ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዱልፈታህ ኢብራሂም በበኩላቸው ጽ/ቤቱ በክልልሉ የሚንቀሳቀሱ ነጋዴዎችን በማስተባባር ለተፈናቃዮቹ የምሳ ግብዣ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም በጽ/ቤቱ በኩል ለተፈናቃዮቹ የሚደረገው ድጋ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተናገሩት፡፡

በሐረሪ ክልል ድጋፍ እየተደረገላቸው የሚገኙ የሁለቱ ክልል ነዋሪዎች የክልሉ መንግስትና ህዝብ ላደረገላቸው ድጋፍና አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ ትህትና  ተስፋዬ

NO COMMENTS