በከተማ ግብርና አነስተኛ መሬት ላይ የተለያየ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት እየተጠቀሙ እንደሚገኙ የሸንኮር ወረዳ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

በከተማ ግብርና አነስተኛ መሬት ላይ የተለያየ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በማምረት እየተጠቀሙ እንደሚገኙ የሸንኮር ወረዳ ነዋሪዎች  ተናገሩ፡፡

አብዛኛውን ግዜ ከተለመደው የእርሻ ግብርና በስተቀር በከተማ በሚገኙ አነስተኛና መጠነኛ መሬቶች ላይ ማምረት አይታወቅም፡፡

 

የሐረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የከተማ ግብርና እንዲስፋፋና ከሌሎች ከተሞች የተገኙት ልምዶች በመውሰድ በከተማ መሬት ላይ የተለያየ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያመርትና ህብረተሰቡ በምግብ ራሱን እንዲችል የዘርፉ አስተዋጾ ከፍተኛ በመሆኑ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

 

በሸንኮር ወረዳ የሚገኙ በከተማ አነስተኛ መሬት ያላቸው አርሶ አደር ነዋሪዎች አትክልትና ፍራፍሬ እያመረቱ መሆናቸውን ለሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ገልፀዋል፡፡

 

የወረዳው ነዋሪ የሆኑት አቶ ያሲን መሀመድ የከተማ ግብርና የጀመሩበትን ሁኔታ እንህ ገልፀዋል፡፡

 

በተለይ ዘርፉ በተለይ ዘርፉ በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ እራስን ለመቻል ጠቃሚ መሆኑ ለስራው ያነሳሳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

ሌላው የወረዳው አርሶ አደር አቶ አብዱሌ ዩሱፍና ወይዘሮ መፍቱሃ ሙሳ ለዘመናት ውሃ ዳር ኖረው አትክልትና ፍራፍሬ አለማምረታቸው እንደቆጫቸው በመግለፅ አሁን ወደ ልማቱ መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

 

ለስራው መሳካት የግብርና ባለሞያዎች የሚደረግላቸው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ነዋሪዎቹ በባለሞያዎቹ በምክርና አስፈላጊ ነገር ሁሉ ለመርዳት ጥረት ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

 

ከሚያመርቱት አትክልትና ፍራፍሬ ጥቅም እያገኙ መሆኑንና ሸጠው ተጨማሪ ብር ከማግኘት ባለፈ ከዚህ በፊት ለአትክልትና ፍራፍሬ ሲያወጡ የቆዩትን ወጪ እንዳስቀረላቸው ተናግረዋል፡፡

 

ነዋሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክትም በወንዝ አጠገብ ያሉ ሰዎች የነሱን ተሞክሮ በማየት ወደ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት እንዲሰማሩ ነው የጠየቁት፡፡

 

በሀረሪ ግብርና ልማት  ቢሮ የከተማ ግብርና ባለሞያ የሆኑት አቶ ፋሲል አህመድ በራሳቸው ተነሳሽነት የከተማ ግብርናና የጀመሩትን አርሶ አደሮች መርጥ ዘር እና ስራው በጅምር ያለ ሲሆን በቀጣ ሁሉም አርሶ አደሮች በመስኖ እንዲሳተፉ ከፍተኛጥረት እያደረግን ነው ብለዋል፡፡

 

የከተማ ግብርና እንዲስፋፋ የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ እቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጻል፡፡

 

ዘጋቢ ዲኔ መሀመድ

12 8 13