በኮቪድ ምክንያት ዘግይቶ የተጀመረው ትምህርት የ1ኛው ወሰን ቆይታውን አጠናቋል፡፡

በኮቪድ ምክንያት ዘግይቶ የተጀመረው ትምህርት የ1ኛው ወሰን ቆይታውን አጠናቋል፡፡

የሳምንቱ የትምህርት ቀናት ባጠረበት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት የሴሚስተር ትምህርት ግዜ እየሄዱበት ያለበት ሁኔታን በተመለከተ የሐረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ቅኝት አድርጓል፡፡

የራስ መኮንን ትምህርት ቤት ምክትል  ርእሰ መምህር አቶ መሀመድ አደም የ2013 ትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ዘግጦ ቢጀመርም ለአንደኛ ሴሚስተር የተሰጠንን ግዜ በማጠናቀቅ በአሁኑ ሰዓት ፈተና ፈትነን አጠናቀን ለተማሪዎች ውጤት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

 

ምንም አንኳን በአንደኛ ውሰነ ትምህርት ሰዓት በግዜ ጥበት ሳቢ ለተማሪዎች ፈተናውን በግዜ አርመን ለመስጠት ተግዳሮት ቢሆንብንም ችግሩን በመፍታት ፈተናው ታርሞ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡

 

ኮቪድን ለመከላከል በትምህርት ቤቱ ውስጥ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደሚደረግ የተናገሩት መምህሩ ከዚህ ውጭ መዘናጋት ስለሚታይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

 

ተማሪ ሀብል ዘሩ የነበረውን የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት ጥሩ እንደነበር ገልፆ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ግዜያቸውን በፕሮግራም ቢጠቀሙ ውጤታማ እንደመሆኑ ነው የተናገረችው ፡፡

 

ተማሪ አዚዛ ሙዲን ሴት ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፆ በተደረገው ድጋፍም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልፃለች፡፡

 

ተማሪዎችም አብዛኛው ግዜያቸውን ከጨዋታ ይልቅ ለትምህርታቸው ቢሰጡ ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ነው የተናገረችው ፡፡

 

በክፍላቸው ውስጥተማሪዎች መምህር በማይኖርበት ግዜ እርስ በእርስ በመማማር እንደሚያሳልፉ ገልፃለች፡፡

 

በቤት ውስጥ ቤተሰቦቼ በትምህርት ውጤታማ እንዲሆን እገዛ ስለሚያደርጉልኝ ውጤታማ መሆን ችያለሁ ብላለች፡፡

 

ዘጋቢ አዳነ ታደሰ 20 7 13