በዛሬው እለት ለብልጽግና ፓርቲ አባል የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች በፓርቲው የፖለቲካና እና አጠቃላይ ፕሮግራም ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል ፡፡

በዛሬው እለት ለብልጽግና ፓርቲ አባል የሆኑ የመንግስት ሰራተኞች በፓርቲው የፖለቲካና እና አጠቃላይ ፕሮግራም ዙሪያ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል ፡፡

ስልጠናው  ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሀረሪ ክልል ም/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አዲስአለም በዛብህ እንደተናገሩት መልካም አስተዳደር ላይ ያለውን ችግር ለመፍታት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል ብለዋል ፡፡

 

የኮቪድ ስርጭት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ስርጭቱን ለመግታት ሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

 

ስልጠናው በዋናነት የብልጽግና ፓርቲ በማሕበራዊ ዘርፍ በጤና ፣ በትምህርት ፣ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ያዘጋጀውን የፓርቲው ፕሮግራምን በተመለከተ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡

 

ለአባላቶቹ እየተሰጠ የሚገኘውን የብልጽግና ፓርቲ ስልጠና ላይ የክልሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

 

ስልጠናው ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 2/2013 ዓ/ም እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዘጋቢ አሚር ኡስማን

29 7 13