በድሬ ጠያራ ወረዳ ከብት እርባታ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸውን ተናገሩ፡

በድሬ ጠያራ ወረዳ ከብት እርባታ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች ውጤታማ መሆናቸውን ተናገሩ፡

አቶ ኢሊያስ አብዱራህማን የድሬ የጣራ ወረዳ ነዋሪ ሲሆኑ አሁን ላይ በከብት እርባታ ላይ ተሰማርዋል፡፡

 

ከዚህ በፊት በሌላ ስራ ተሰማርተው የነበሩት አቶ ኢሊያስ ከመንግስት ባገኙት ብድር አምስት አባላት ያለው ማህበር አቋቁመው ወደዚህ ስራ መግባታቸውን ተናግረው  በአሁኑ ሰዓት ወተት ለገበያ በማቅረብ የወተት ከብት ቁጥርም በማባዛት ላይ እንደሚገኙ ነው የገለፁት ፡፡

 

በከብት ወተት ብቻ ወርሃዊ ገቢ እስከ 60 ሺ ብር እያገኙ እንደሚገኙና  ወደገበያም ከብቶችን እንደሚያቀርቡ ገልፀዋል፡፡

 

ይሁን እንጂ እነዚህ ከብቶቸን ምግብ መመገቡ እየከበዳቸው መምጣቱን ያነሱት ወጣቶቹ ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ትብብር እንዲያደርግባቸው ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

 

የድሬ ጠያራ ወረዳ ለከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለከተማው ማህበረሰብ  ወተት ለማቅረብ አመቺ መሆኑን በማረጋገጥ  ክትትል እያደረግን ነው ያሉት በሀረሪ ክልል የገጠር ስራ እድል ፅህፈት ቤት አንድ ማእከል ሀላፊ አቶ ሙራድ ኢብራሂም ናቸው ፡፡

 

 በመጨረሻም ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች ተስፋ ከመቁረጥ ወተው በትኩረትና ቁርጠኝነት  ስራን ሳይንቁ መስራት ይገባቸዋል  ብለዋል፡፡

 

ዘጋቢ ትህትና ተስፋዬ

21 7 13