በጀኔላ ወረዳ በሸዋበር መናኸሪያ ውስጥ የብርና የቁስ ዝርፊያዎች መበራከታቸውን አንዳንድ በቦታው ያነጋርናቸው ተሳፋሪዎች ለሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ገለፁ፡፡

በጀኔላ ወረዳ በሸዋበር መናኸሪያ ውስጥ የብርና የቁስ ዝርፊያዎች መበራከታቸውን አንዳንድ በቦታው ያነጋርናቸው ተሳፋሪዎች ለሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ገለፁ፡፡

ሆኖም ግን ይህን በዝርፊያ ወንጀል ለመከላከል እየተሰወደ ያለው እርምጃ ሲለካ ግን እዚህ ግባ አይባልም፡፡

 

በሀረር ከተማ በጀንኤላ ወረዳ በሸዋበር መናኻሪያ ውስጥ በብርና በቁስ ዝርፊያ ምክንያት እንደተቸገሩ አንዳንድ በቦታው ያነጋርናቸው ተሳፋሪዎች ገልጸዋል፡፡

 

ተሳፋሪዎች እንዳሉት የኑሮ ውድነቱና  ስራ አጥ መብዛቱ ስርቆት እንዲበራከት መንስኤ መሆኑን አንስተዋል፡፡

 

ለዚህም የሚመለከተው አካል የወንጀል ድርጊቱን ለመቆጣጠር በሰፊው መሥራት አለበት ሲሉም ገልጸዋል፡፡

 

የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲም ጉዳዩን በማስመልክት ከጀኔላ ወረዳ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ያሲን ሀሰን ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

 

አቶ ያሲን በቆይታቸው እንደገለፁት በመነሀሪያ ውስጥ የሚከናወኑ የዝርፊያ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በካሪ ሥራ የተሰማሩትን የማሕበረሰብ አቀፍ ፖሊስ በማቀናጀት እና የፖሊስ ተባባሪ ሆነው እንዲሰሩ በማድረግ ስርቆትን ለመከላከል እየሰሩ እንደሚገኝ አስረድተዋል

 

በዘርፉ ያሉትን ክፍተቶች ወረዳው ከልሶ የማስተካከያ አቅጣጫ በማስቀመጥ እንደሚሰራም አቶ ያሲን አስታውቀዋል፡፡

 

ዘጋቢ ኢሊያስ መሀመድ

30 7 13