በጄኔላ ወረዳ የመራጮችን ምዝገባ የወሰዱ ዜጎች ቁጥር በሚጠበቀው ልክ አይደለም ተባለ ፡፡

በጄኔላ ወረዳ የመራጮችን ምዝገባ የወሰዱ ዜጎች ቁጥር በሚጠበቀው ልክ  አይደለም ተባለ ፡፡

በሀረሪ ክልል የጅኔላ ወረዳ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ምዝገባ ሹም ወይዘሪት ሀና ደሳለኝ የመራጮች ምዝገባን በሚመለከት ከሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ህብረተሰቡ ዲሞክራሲያዊመብቱን ተጠቅሞ ይበጀኛል ብሎ የሚያምንበትን ፓርቲ በ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በነቂስ ወጥቶ ሊመርጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 

በወረዳው የሐረሪ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሊሰራ እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡

 

የጅኔላ ወረዳ ምርጫ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ ሱራፌል ይግዙ በበኩላቸው ከመጋቢት 24 ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ ቢጀምሩም  የተመዝጋቢው ቁጥር እምብዛም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በጅኔላ ወረዳ በተለይም በቀበሌ 14 ልዩ ስሙ ቦቴ አካባቢ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡

 

ለ6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የቀረው ትንሽ ግዜ በመሆኑ ህዝቡ የምርጫ ካርድ በመውሰድ በእድሉ ሊጠቀም እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

 

ዘጋቢ አሚር ኡስማን

12 8 13