በ6ኛው ሀገራዊ9 ምርጫ ወቅት ብዙኃን መገኛኛ ተቋማት በኃላፊነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በ6ኛው ሀገራዊ9 ምርጫ ወቅት ብዙኃን መገኛኛ ተቋማት በኃላፊነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሸኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረውን 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ በመጪው ግንቦት 28 ለማካሄድ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል ፡፡

 

የሀገሪቱ የምርጫ አዋጅ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡ከዚህም ውስጥ የመገኛኛ ብዙኃንና የጋዜጠኞችን የምርጫ አዘጋገብ  የሥነ ምግባርና አሰራርን መመሪያ መጥቀስ ይቻላል፡፡

 

ማሻሻያው መገናኛ ብዙኃን በተለያየ የምርጫ ወቅት በኃላፊነት ሚናቸውን መወጣት ላለባቸው ጉዳይ ዙሪያ ያተኩራል፡፡

 

   በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው ጋዜጠኞች መካል የድሬደዋ መገኛኛ ብዙኃን ጋዜጠኛ የሆኑት ሙሉአልም ሰለሞን በምርጫ ወቅት ብዙኃን መገኛኛ ተቋማት በሀላፊነት መንቀሳቀስም ሆነ ለሕብረተሰቡ  የመምረጥ መብቱን ተግባራዊ እንዲያደረግ መረጃ በመስጠት ሊያግዙ እንዲገባ ገልጸው ምርጫው ዜጎች ዲሞክራሲዊ መብታቸውን የሚተገብሩበት አንድ እድል በመሆኑ መገኛኛ ብዙኃን ትክክለኛ ወቅታዊና በቂ መረጃ በማቅረብ ሚዛናዊ ገለለግተኛ በሆነ መልኩ ትክክለኛ መረጃን ማድረስ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

 

የመገኛኛ ብዙሀን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ እንደመሆናቸው መጠን መረጃን ማቀበልና ስለምርጫ ሂደቱ በቂ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ተቁመው በመጪው 6ኛ ሀገራዊ ምርጫ እንደ ጋዜጠኛ ኃላፊነታችንን በመወጣትና ሙያዊ ስነ ምግባርን በተከተለ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የጠቆሙት የሀረማያ ፋና ኤፍ ኤም 90.8 ጋዜጠኛ የሆኑት እዮናዳብ አንዱአለም ናቸው፡፡

 

ሌላኛው የሀረማያ ፋና ኤፍ ኤም 90.8 የፕሮግራም ክፍል ኃላፊ የሆኑት ጋዜጠኛ ተሾመ ሓይሉ ምርጫው  ሰላማዊና ዲሞክራሲዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጋዜጠኛው ሚና የላቀ መሆኑን ጠቅሰው ሀገራችን ለውጥ ላይ እንደመሆኗ መጠን ሕብረተሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ ጋዜጠኞች ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 

የጆን ሆፕኪንስ ሴንተር የኮምኒኬሽን ባለሞያና የፕሮግራም ዲዛይን እና ኢኖቬሽን ዳሬክተር የሆኑት አቶ ብሩክ መላኩ ፍትሀዊና ሰላማዊ ምርጫ ለማድረግ የመገናኛ ብዙኃን ድርሻ የጎላ መሆኑን በመጥቀስ የመገኛ ብዙኃን ከወገንተኝት በጸዳ መልኩ ለሕረተሰቡ ትክክለኛ መረጃን የማድረስና ስህተቶችን በማንሳት የመፍትሄ ሐሳቦችን በመጠቆም ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የጥላቻ የሐሰትና ሚዛናዊ ያልሆኑ መረጃዎችን በማሰራጨት ረገድ በተለይ በማሕራ ሚዲያው ላይ ስለሚስተዋሉ በምርጫው ወቅት ማሕበረሰቡ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲሚገባው እና ለሚሰራጨው መረጃ ኃላፊነትን መውሰድ የሚችሉና ተጠያቂነት ያለባቸው የማሕበራዊ ትስስር ገጾች የትኞቹ ናቸው ብሎ መለየት ከተደራሲኑ የሚጠበቅ መሆኑን መክረዋል

አያንቱ አህመድ

29 7 13