ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየው የማስክ አጠቃቀም አናሳ መሆኑን የሀረሪ ክልል ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ባደረገው ቅኝት ለመታዘብ ችሏል፡፡

ትምህርት ቤቶች ላይ የሚታየው የማስክ አጠቃቀም አናሳ መሆኑን የሀረሪ ክልል ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ባደረገው ቅኝት ለመታዘብ ችሏል፡፡

ይህ ችግርም በትምህርት ላይ የሚገኙ አመራሮች ቁርጠኝናትና የክትትል ማነስ መሆኑ የክልልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

 

ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር አንስቶ ላለፉት 8 ወራት ትምህርት ቤቶች በዚሁ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዘግተው እንደነበር የሚታወስ ነው

 

   የትምህርት ቤቶች መዘጋት ያለው አሉታዊ ተጽኖ ከፍተኛ በመሆኑ እንደ ሀገር አቀፍ በተቀመጠ አቅጣጫ መሠረት በሽታውን እየተከላከሉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል የተቀመጡ መመሪያዎች በመከተል ትምህርት ቤቶች እንደገና ሊከፈቱ ችለዋል፡፡

 

   እነኝህ መመሪያዎችን በመከተል እንደ ክልል መሟላት ያለባቸውን የመከላከለያ ቁሳቁሶች በሟሟላት ትምህርት እዲጀመር መደረጉን የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብይ አበበ አስታውሰዋል፡፡

 

  ትምህርት ቤቶቹን ስናስጀምር አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በሟሟላትና መደረግ ያለባቸውንና መደረግ የሌለባቸው ጉዳዮች በመመሪያ መልክ በማስቀመጥ ነው ያሉት ም/ቢሮ ኃላፊው ትልቁ ችግር እንደ መመሪያ የተቀመጡትን አለመተግበር ነው ብለዋል፡፡

 

ትልቁ ተግዳሮት ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ሲወጡ ማሕበረሰቡን እንደመቀላቀላቸው መጠን በማሕበረሰቡ ዘንድ የሚታየው የአፍና አፍንጫ አጠቃቀምና ትኩረት አናሳ መሆኑ ነው ይላሉ፡፡

 

ማንኛውም ሰው አካል ወደ ትምህርት ቤቶች ሲመጣ የፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል  ማድረግ ግዴታ ነው የሚሉት አቶ አብይ ይህ ቢሆንም ግን ወደ ትምህርት ቤቶች ለመግባትና አገልግሎት ለማግኘት ብቻ ጭንብል የመጠቀም ልምድ እንዳለም ይናገራሉ፡፡

 

እንደ ክልል ትምህርት ቤቶችን ስናስጀምር ላሉን ከ57 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ማስክ በማደል ነው ያሉት ም/ቢሮ ኃላፊው ይህ ቢሆንም ግን ማስክ በአግባቡ ያለ መጠቀም ልምድ ተስፏፍቷል ይላሉ፡፡

 

የሀረሪ ክልል ብዙኃን መገኛኛ ኤጀንሲ የመስክ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ይህንን ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

 

ክፍተት የሚታይባቸው አንዳንድ ትህርት ቤቶች ቢኖሩም  በመስክ ምልከታችን ካየናቸው ትምህር ቤቶች መካከል የጀግኞችና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ጥሩ የሚባል የማስክ አጠቃቀም እንዳለ ለመታዘብ ችለናል፡፡

 

ታዲያ ይህ ልዪነት እንዴት ሊመጣ ቻለ በሚልም ም/ቢሮ ኃላፊውን አቶ አብይ አበበን ጠይቀናል፡፡

 

የተማረው ማሕበረሰብ ክፍል ፣ መምህራኞች እንዲሁም ተማሪዎች ለሌላው አርአያ መሆን ስላለብን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል በመጠቀም በምንቀሳቀስበት ወቅት ሁላችንም ማስክ አድርገን መንቀሳቀስ አለብ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

እዩኤል ጸጋዬ

28 7 13