አቶ በክሪ አብዱላሂ በ62 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

0
309

አቶ ብክተሪ ከ1991 ጀምሮ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮን በዋናና በምክትል ስራ አስኪያጅነት መርተዋል፡፡
አቶ ብከሪ አብዱላሂ ከአባታቸው አቶ አብዱላሂ መሀመድ እና ከእናታቸው ወ/ሮ ሀቢባ አሊ በ1947 ዓ.ም ነበር ይህችን አለም የተቀላቀሉት፡፡
እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰም የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሀረማያ እና በሀረር መድሃያለም ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡
በ1976 በአዝእርት ሳይንስ ቴክኖሎጂ ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ዲፕማቸውን ያገኙት አቶ በክሪ በ1991 ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በህግ ድግሪያውን አግኝተዋል፡፡
አቶ በክሪ በተለያዩ የስራ ዘርፎች አገራቸውንና ወገናቸውን በቅንነትና በታማኝነት ያገለገሉ ሲሆን በዋንኛነት ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮን በዋናና በምክትል ስራ አስኪያጅነት መርተዋል፡፡
ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ የቆዩት አቶ በክሪ በ62 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
የቀብር ስነ ስርዓታቸው በዛሬው እለት ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት በአው አብዳል ተፈፅሟል፡፡
አቶ በክሪ የሁለት ሴቶችና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ፡፡
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ፣ የክልሉ መንግስትና የሀረሪ ብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ በአቶ በክሪ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን በመግለፅ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፤
ሰይድ አብዱልቀዪም
05.11.09

NO COMMENTS