አቶ አሪፍ አብዱልሃፊዝ በ50 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡

0
217

አቶ አሪፍ በሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮና በሀረር ብድርና ቁጠባ ተቋም በሃላፊነት የሰሩ ሲሆን እስከ እልፈተ ህይወታቸው ድረስም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
አቶ አሪፍ አብዱልሀፊዝ ከአባታቸው አብዱልሀፊዝ ሙኒር እና ከእናታቸው ከዱጅ መሀመድ አብደላ በ1959 ሀረር ከተማ ተወለዱ፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአባድር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሀረር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡
የከፍተኛ ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የተከታተሉ ሲሆን በኢኮኖሚክስ የትምህርት ዘርፍም ተመርቀዋል፡፡
አቶ ሀሪፍ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲሆን በዋነኝኘትም የሀረሪ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮና የሀረር ብድርና ቁጠባ ተቋምን በሀላፊነት መርተዋል፡፡
እስከ ህልፈት ህወታቸው ድረስም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡
ስራ ወዳድና ሰው አክባሪ የነበሩት አቶ ሀሪፍ የ3 ወንድ እና የ 1 ሴት ልጅ አባት ነበሩ፡፡
በደረሳባቸው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሀምሌ 3 ቀን 2009 ዓ.ም በ50 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
በዛሬው እለትም በሀረር አው አብዳል ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ቀብር ስነ ስርዓታቸው ተፈጽሟል፡፡
የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ፣ የክልሉ መንግስትና የሐረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲም ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
ዘጋቢ ሰይድ

NO COMMENTS