ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ዙርያ የያዘችውን አቋም በመቀጠል በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብትን ማረጋገጥ አለብን ሲሉ የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ዙርያ የያዘችውን አቋም በመቀጠል በአባይ ወንዝ የመጠቀም መብትን ማረጋገጥ አለብን ሲሉ የሀረር ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ አስር አመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ግድቡ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ የመንግስት ቁርጠኛ አቋም እና ህዝባዊ ተሳትፎ የአሻራው ምሰሶና የግንባታው ደጀን ሆኖ ለዚህ ደረጃ አብቅቶታል፡፡

 

እንደ ሀገር ግድቡን አሁን ላለበት  ለማብቃት ብዙ ፈተናዎች እና ረጅም መንገዶችን ብንጓዝም የግድቡ አፈፃፀም ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ሲደርስ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት እንቅፋት ጨመረ፡፡

 

ታዲያ በዚህ የለውጥ ጉዞ የግድቡ ግንባታ እጅ የተፋጠነበት እና የህዝቡ ድጋፍ እጅጉን የተጠናቀረበት ነበር፡፡

 

ይህ ቢሆንም ግን የታችኛው የተፋሰስ ሀገራት ተፈጥሮ ያጎናፀፈችንን የተፈጥሮ መብት እንዳንጠቀም የሚያደርጉት ትግል  አሁንም እንደቀጠለ ነው ፡፡

 

ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህን ለማስጠበቅ ቆፍጠን ያለ አቋም ይዛ እየተጓዘች ትገኛለች፡፡

 

ከዚህ ባለፈ የሶስትዮሽ ጥቅምን ያማከለ እና ፍትሀዊ አጠቃቀም ለማረጋገጥ ከተፋሱ ሀገራት ጋር የተለያየ ድርድሮችን ስታደርግ ብትቆይም የተፋሰሱ ሀገራት የራስ ጥቅምን ማስቀደማቸው ያለስምምነት ተጠናቋል፡፡

 

በተለይ ግብፃዊያን  አሁን ላይ እያነሱት  ያለው ሀሳብና ዛቻ መሠረተቢስ ነው የሚሉት የሀረር ከተማ ነዋሪዎች የህዳሴው ግድብ የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን  ከሉዓላዊነት ጋር የሚገናኝ  በመሆኑ ህዝብ ጠንካራ አቋም ሊኖረው እና አሻራውን ማሳረፍ ይኖርበታል ይላሉ፡፡

 

ምንም እንኳን ግብፃዊያን ጦርነት ጦርነት  የሚሸቱ ዛቻዎችን እየነዙ ቢገኙም እኛ በዲፕሎማሲ መንገድ፤በሰላም መፈጸም መቻል አለብንም ባይ ናቸው፡፡

 

እስካሁን ከታችኛው የተፋሰስ  ሀገራት ጋር የተደረጉ  ድርድሮች ያለ ስምምነት ቢጠናቀቁም የግድቡ ግንባታ ለአፍታ እንኳን ሳይቆም መቀጠል አለበት የሚሉት እነሱ ድጋፋችን ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተናግረዋል፡፡

 

የግድቡ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት ባለፈው አመት የተካሄደ ሲሆን ሁለተኛው ዙር ደግሞ በመጪው ክረምት ሐምሌ ይካሄዳል፡፡

 

 የግድቡ ግንባታ ባጠቃላይ 80 በመቶ መጠናቀቁንና ቀሪው 20 በመቶ በተያዘለት የግዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሰራም ይገኛል፡፡

 

ዘጋቢ እዩኤል ፀጋዬ

12 8 13