እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት የመውጣት ጥያቄ በዜጎቿ ላይ አንዳንድ መብቶች  ሊያነሱ እንደሚችሉ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ፡፡

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷ ተከትሎ በሀገሪቱ በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች እየገጠማት ይገኛል፡፡

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷ ለሀገሪቱ እንግሊዝ እና ለአውሮፓ ህብረት በአጠቃላይ ልዩ ክስተትን የፈጠረ እና የአውሮፓ ህብረት አንድነት እና ጥንካሬ የተፈታተነ ህዝብ ውሳኔ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የእንግሊዝ ህዝብ ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት እንድትወጣ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ ያሰለፉ ቢሆንም የሀገሪቱን ከፍተኛ አመራሮች እንግሊዝ ከህብረቱ ሙሉ በሙሉ አሊያም በከፊል ትውጣ በሚለው  ጉዳይ ላይ ግን ከውሳኔ መድረስ አልቻሉም፡፡

የቀድሞ የቤልጄም ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ጌይ ቬርሆፍ ስታዴት ዘጋርዲያን ላይ ባሰፈሩት ጹሁፍ ቴሬዛ ሜይ የሀገራቸውን ዜጋ መብት በአውሮፓ ህብረት እንዲጠበቅላቸው ከፈለጉ ለህብረቱ የሚያቀርቡትን ጥያቄ ሊያሻሽሉ ይገባል ብለዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት  ዜጎች በእንግሊዝ ምድር  አንዳንድ መብቶቻቸውን ሊነፈጉ ይችላሉ ያሉት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር በሌሎች የሀገራቸው ባለስልጣናትም ድጋፍ እያገኘ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህ የቀድሞ ጠቅላ ሚኒስቴር ሀሳብ አራማጆች መካከል አንዱ የሆኑት የቤልጄም ፓርላማ አባል የሆኑት ፈሊፕ ላምባርትስ አውሮፓ ህብረት ለእንግሊዛውያን የሚሰጠው የዜግነት መብት ሶስተኛ የዜግነት መብት ደረጃ ነው ብለዋል፡፡

እንግሊዝ ደግሞ በማንኛውም ግዜ ሊሻር የሚችል የሁለተኛነት የዜግነት መብት ለአውሮፓ ህብረት ዜጋዎች   የምትሰጠው  ነው  ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ይህ የቤልጄም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀሳብ ግን የቴሬዛሜይ መንግስት አባል የሆኑት ደማያን ግሪን የተሳሳቱ እሳቤ በማለት አጣጥለውታል፡፡

አውሮፓውያን በእንግሊዝ ሀገር ሆነው የመስራት መብታቸው የተጠበቀ ቢሆንም ምቹ የስራ ሁኔታ ስለ ማይኖር እንግሊዝ ሀገር ከመስራት በሌሎች ሀገራት መስራትን ሊመርጡ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ይህ ደግሞ በዋነኝነት የሐገሪቷን ኢኮኖሚን እንደሚጓዳው ነው የሚነገረው፡፡

እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት መውጣቷን ተከትሎ በቀጣይ በበርካታ ርዕስ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ይካሄዳል ተበሎ ይጠበቃል፡፡

ዩሮ ኒውስ ዘገባን በሀር ጠንክር እንዳዘጋጀው፡፡

NO COMMENTS