ከከተማ ተቋማት መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተገኙ 5 የውሃ ቦቴዎችን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለክልሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን እና ለሌሎች ተቋማት አስረከቡ፡፡

ከከተማ ተቋማት መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም የተገኙ 5 የውሃ ቦቴዎችን የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለክልሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን እና ለሌሎች ተቋማት አስረከቡ፡፡

   የከተማ ተቋማት እና መሰረተ ልማት መስፋፊያዎች ፕሮግራም የሀረር ከተማ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የሀረር ከተማን የውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት ለማሻሻል 25 ሚሊየን የሚያወጡ 5 የውሃ ቦቴዎችን ለክልሉ ውሃነ ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን በድጋፍ መልክ አበርክቷል፡፡

 

በዛሬው እለት በሀረሪ ክልል ርዕስ መስተዳድር አማካኝነት ለሀረር ከተማ ለመጠጥ ፣ ለአረንጋዴ ልማትና ድንገተኛ አደጋን ለመከላከል ለውኃ አቅርቦት አገልግሎት የሚውል በሀረር ከተማ UIIDP  ፕሮግራም ማስተባሪያ ጽ/ቤት የተገዙ 3 የውሃ ቦቴ ተሸከርካሪዎች ለውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፣ 1 ለእሳት አደጋ መከላከልና 1 ለአረንጋዴ ሥፍራ መንከባከቢያ አስረክበዋል፡፡   እንዲሁም የሸንኮር ወጣች ማዕከል ግንባታ G +4 የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧልሠ፡፡

 

በተጨማሪም ሸንኮር መንገድ ማስፋፊያ እየተሰራ ያለውን ድልድይም ጎብኝተዋል፡፡

 

በርክክብ መርሀ ግብሩ ላይ የሀረሪ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በዚሁ ወቅትም የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለፁት የክልሉ የመጠጥ ውሃ ችግርን ለመቅረፍ ከተለያዩ አካላት ጋራ በመቀናጀት ሥራዎች እየተካሄዱ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

 

በሌላ በኩል ርዕስ መስተዳድሩ አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉን የውሃ ችግር ለመፍታት የረጅም ጊዜ እቅድ ይዞ መስራት ቢያስፈልግም ለጊዜው ያለውን ችግር በፍትሀዊነት መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

 

የከተማው ማዘጋጃ ቤትም ከ UIIDP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በክልሉ ያለውን የመሰረተ ልማት ችግር ለመቅረፍ ያደረጉት ርብርብ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

ድጋፉ ለአረንጋዴ ልማት ቀጣይነት፣ ለተፈጥሮ አደጋዎች ፣ ለእሳት  አደጋና በተለያዩ ጊዜዎች የሚከሰቱ ችግሮችን ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡

 

በሌላ በኩል ፕሮጀክቱ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራና ለመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ በመሆኑ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

 

በፕሮጀክቱ የመንገድ፣ የመብራት ፣ የዲችና በሕረተሰብ የሚነሱ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን መሠረት ያደረጉ ሥራዎችንም እንደሚያከናውኑም ገልጸው ለክልሉ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለሥልጣን የተበረከቱትን ቦቴዎች በባለቤትነት ስሜት መጠቀም እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

 

ከዚህም ጋር በተያያዘ ርዕስ መስተዳድሩ ለሸንኮር ወጣቶች ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

 

የመሰረት ድንጋዩን ባስቀመጡበት ወቅት እንደገለፁት በሸንኮር ወረዳ እየተሰራ ያለውን የመሠረተ ልማትና የመንገድ ማስፋፋት ሥራ ሕብረተሰቡ ላሳየው ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበው ለወጣቶች ማዕከል ግንባታ የተጣለው የመሰረት ድንጋይ የወጣቱን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

 

አክለውም ሸንኮር ላይ የሚሰራው የወጣቶች ማዕከል እስካሁን ተገንብተው አግልግሎት እየሰጡ ካሉ የወጣት ማዕከላት በጣም የተለየና ደረጃውን የጠበቀ የተለያዩ የመዝናኛ አይቶች ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

 

በተጨማሪም ወጣቱ ከአልባሌ ሥፍራ ከመዋል ተቆጥቦ እራሳቸውንም ሆነ ሀገራቸውን ሊጠቅሙ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

 

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱከሪም በበኩላቸው እንደገለጹት ወጣቶች ከአልባሌ ሥፍራዎች ውሎ ለማላቀቅ የወጣቶች ማዕከል ግንባታዎች ማስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡

 

ርዕስ መስተዳድሩ አክለውም ግንባታዎችን መጀመር ብቻ ሳይሆን ማጠናቀቅምና የተጀመረውንም ከዳር ለማድረስ የሚመለከተው አካል ሁሉ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

ሂዳያ ፉአድ

28 7 13