ወደ ሳተላይት ለመውጣት የቅድመ ዝግጅት ሥራውን እያጠናቀቀ መሆኑን እንደሆነ የሀረሪ ክልል ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡

ወደ ሳተላይት ለመውጣት የቅድመ ዝግጅት ሥራውን እያጠናቀቀ መሆኑን እንደሆነ የሀረሪ ክልል ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡

በዚህ መሠረትም ወደ 80 የሚሆኑ የተለያዩ ይዘቶች ተቀርጸው ግምገማ እየተደረገባቸው ነው የተባለ ሲሆን በቴክኒክ ዘርፉም ዘመን ያፈራውን ቴክኖሎጂ ለመታጠቅ ብዙ ርቀት ተኪዳል ተብላል፡፡

ኤጀንሲው ከመንግስት ከሚበጀትለት በጀት ባሻገር ራሱን በገቢ ለመቻል በሚያደርገው ጥረት ውስጥም የተለያዩ ለማስታወቂያ የሚሆኑ ዘመናዊ ድሮኖችን ጨምሮ ካሜራዎችና ኮምቲዩተሮችን  ለግዛት ስለመታቀዱ ተነግሯል፡፡

በኤጀንሲው በኩል እንደ ሀገር የተሻለና ተወዳዳሪ ሚዲያ ለመሆን በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ያሉት የኤጀንሲው ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱረህማን አሰፋ ሰራተኛውም በተለይ ደግሞ ጋዜጠኛው እራሱን ማዘጋጀት አለበት ብለዋል፡፡

በዚህም የሀረሪ ቴሌቪዥን ስርጭት የይዘት ዘርፍ የዝግጅት ስራዎች፣ የሙከራ ስርጭት ዝግጅት፣ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባት እና የስርጭት ፍቃድ ሁኔታን በተመለከተ ለሰራተኞች ገለጻ ተደርጓል፡፡

የሀረሪ ብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ በኢንተርኔት አማካኝነት በፈንጆቹ ግንቦት 1 የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀምርም አቶ አብዱረህማን ተናግረዋል፡፡

ሄኖክ ዘነበ

4 8 13