ዕድሜያው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው የሕረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት ሊሰጥ መሆኑ የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

ዕድሜያው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው የሕረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት ሊሰጥ መሆኑ የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡

 የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ በሁለተኛው ዙር እድሜያቸው

 

 ከ65 በላይ ለሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው የሕበረተሰብ ክፍሎች የኮቪድ 19 ክትባት ለመስጠጥ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቀ፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለው የኮቪድ 19 ስርጭት ለመከላከል በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠይቅ የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ኢብሳ አብራሂም ገልጸዋል፡፡

 

ስርጭቱን የሕረተሰቡ እንቅስቃሴ በሚበዛበት መንግስዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ፣ ቤተ እምቶችና ትህርት ቤቶችና የመሳሰሉ አካባቢዎች ላይ የሰዎችን እንቅስቃሴ በመቀነስ ስርጭቱን ለመቆጣጠር ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በቀጣይ 6ኛው ሀገር ምርጫና ከረመዳን ወር ጋር ተያይዞ የሰዎች እንቅስቃሴ ስለሚጨምር ሕብረረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቅቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ መስጠት ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በሁለተኛው ዙር የክትባት ጊዜ ዕድሜያቸው ከ65 በላይ ለሆኑና ተጓዳኝ በሽታ ላለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባት ለመስጠጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አቶ ኢብሳ ገልጸዋል፡፡

 

ክትባቱ ሲጀመር ሕብረተሰቡ ያለ ምንም ፍርሃት መውሰድ እንዳለበትም አክለው ገልጸዋል፡፡

 

ክትባቱ በአለም ደረጃ ተፈላጊና ዋጋውም ከፍተኛ የሆነ ነው ያሉት ኃላፊው መንግስት ሁሉንም ሕብረተሰብ በየደረጃው ለመከተብ የተለያዩ ጥረቶች እያደረገ ነው ብለዋል፡፡

 

በአሁኑ ጊዜ በኮቪድ 19 ከፍተኛ ስርጭት እየሞተ ያለው ሰውም ቁሩ እየጨመረ ስለሆነ ሕብረተሰቡ ስርጭቱን ለመከላከል የወጣውን መመሪያ ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል ፡፡

 

ዲኔ መሀመድ

5 8 13