የሀረማያ ዩኒቨርስቲ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚያስችል ለ1 አመት የሚቆይ መርሀ ግብር /ፕሮጀክት / ይፋ አደረገ ፡፡

የሀረማያ ዩኒቨርስቲ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚያስችል ለ1 አመት የሚቆይ መርሀ ግብር /ፕሮጀክት / ይፋ አደረገ ፡፡

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ሪድዋን አህመድ በሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሕይወት ፋና እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማህጸንና ጽንስ እስፔሻላይዝድ እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ሲሆኑ የዚህ መድረክ ዋንኛ አላማ የእናቶች ሞት ከመብዛቱ የተነሳ እየተለማመድነው ነው ያለነው ችግር ሆኗል፡፡

 

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያገለግል ፕሮጀክት ለማብሰር መድረኩ መዘጋጀቱን  ተናግረዋል፡፡

 

ዶ/ር ሪድዋን አክለውም የእናቶች ሞት ዋንኛ ምክንያት እናቶች ወደ ጤና ተቋማት ለመውለድ ሲሄዱ ከሪፈራል ጀምሮ የሚደረጉ ቅብብሎሽ ስርአት በወሊድ ወቅት የሚፈስ ደም እና የጤና ባለሞያዎች ትኩረት ማነስ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

 

ይህንን ችግር ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር እንዲሁም ካደጉ ሀገራት ጋር ልምድና ተሞክሮ ለመውሰድ ተግባራዊ ለማድረግ የታሰበ ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በመድረኩም የእናቶች ሞትን በተመለጀተ ከ2000 – 2013 አመት በቀርሳ ፣ በሐረማያና በሐረር ያሉ ሁኔታን በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡

 

ጥናታዊ ጽሁፉን ያቀረቡት ደ/ር መርጋ ዴሬሳ በሀረማያ ዩኒቨርሲሰቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሀረርጌ የጤና ስነ ሕዝብ ስርአት ቅኝት ሐላፊ እንዳሉት    ከጤና ጋር ተያይዞ የእናቶችና የሕጻናት ሞት በብዛት እንደሚያጋጥማቸው ጠቅሰዋል፡፡

 

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥም እናቶች ቤት ውስጥ በወሊድ ጊዜ በመቆየት፣ በመድማት ፣ኢንፌክሽና ፣ በደም ማነስና በደም ግፊት ወደ 938 እናቶች እንደሞቱና ከነዚህም ውስጥ 200 የሚሆኑት በወሊድ ምክንያት እንደሞቱ ተናግረዋል፡፡

 

ደ/ር አበራ ቀናይ በጤናና ሳይንስ ኮሌጅ ውስጥ ድህረ ምረቃው አስተባባሪና የእናቶች እና ህጻናት ረዳት ፕሮፌስር እንዳሉት  ይፋ የተደረገበት ፕሮጀክት ከተለያዩ ምስራቁ ክፍል የሚገኙ የጤና ባለሞያዎች የተሳተፉበት መሆኑን ገልጸው ወደ ፊት ለሚያጋጥመን ሰፊ ስራዎች ቅንጅታዊ አስራሮችን በመፍጠር የእናቶችን ሞት ለመቀነስ አጋዥ እንዲሆን የታሰበ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

አክለውም ደ/ር አበራ የሀረማያ ዩኒቨርሲሰቲ ባለሞያዎችን በማሰልጠን በምስራቅ ኢትዮጲያ ያሉትን በጥናት በመለየት ሰፊ ሥራዎችንእያካሄዱ እንዳለተናግረዋል፡፡

 

በመደረኩ የሀረሪ ክልል ቢሮ ኃላፊዎች፣ የድሬደዋ ጤና ካውንስል ቢሮ ኃላፊዎች. የመስራቅ ሐረረጌና የጤና ጽሕፈት ቤት ሐላፊዎች እንዲሁም የሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተሮች በውይይቱ ተሳትፈዋል፡፡

 

ትህትና ተስፋዮ

5 8 13