የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችን በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ አወያይተዋል፡፡

0
486

ሀረር በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያገኘችበትን የመቻቻል እሴትን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎችን ህብረተሰቡ ሊያወግዛቸው እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ ገለጹ፡፡

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሃዲ የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎችን በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ አወያይተዋል፡፡

4.1.2010

መድረኩን ሲመሩት የነበሩት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ እንደተናገሩት ሀይማትንም ሆነ ብሄርን ምክንት በማድረግ የሀገሪቱን ሰላም ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ሀይሎችን ማንምም እንደማይወክሉ አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጽያ ሱማሌና እና በኦሮሚያ ክልል መካከል የተፈጠረው አለመግባባትም በምን መልኩ መፍታት ይቻላል በሚለው ዙሪያ ለመወያየት መድረኩ መዘጋጀቱንም ገልጸዋል፡፡

ሰላም ታውኮ በሰላም መኖር ሰላማይቻል የሀይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች  ለሰላም መስፈን አይነተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በመድረኩ የተሳተፉ  የሀገር ሽማግሌዎች እንደተናገሩት ሰላም ለአንድ ሀገር እድገት እና ልማት የጀርባ አጥንት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሰሞኑም በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሱማሌና ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመቅረፍ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች ከሁለቱ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት በማድረግ እርቅ ለመፍጠር ማሰባቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ከሁለቱ ክልሎች ተፈናቅለው ወደ ክልሉ ለመጡት ዜጎችም አፎቻዎች ከክልሉ ንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር የምግብ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

ይህን ሲያዳምጡ የቆዩት ርእሰ መስተዳድሩ በሁለቱ ክልሎች መካከል እርቅ ለመፍጠር የሀገር ሽማግሌዎች ኮሚቴ አቋቁመው ከፌደራል መንግስት ጋር በመሆን እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጠር ተናግረዋል፡፡

የሀገር ሽግሌዎች ሰላም እንዲሰፍን በሚያደርጉት ጥረት ውስጥም የክልሉ መንግስት ከጎናቸው እንደማለይ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ኢሊያስ አርጋው

4.1.2010

NO COMMENTS