የሀረሪ ክልል የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶውን አስተዋውቋል፡፡

የሀረሪ ክልል የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶውን አስተዋውቋል፡፡

የሀረሪ ክልል የነጻነትና እኩልንት ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤው ላይ ለእጩ ተወዳዳሪዎች፣ ለምርጫ አስተባባሪዎችና ለስራ አስፈጻሚዎች የፓርቲውን የምርጫ ማኒፌስቶን አስመልክቶ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

 

የሀረሪ ክልል ነጻነትና እስኩልንት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ መሀመድ   ሀሰን የፓርቲውን የምርጫ ማኒፌስቶ ማስተዋወቅ የተፈለገበት ዋና አላማው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊና በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነት ያለው ስኬታማ ምርጫ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ ለማበርከት ነው ብለዋል፡፡

 

ከዚህም በተጨማሪ የፓርቲው የምርጫ ማኒፌስቶ አካታችነትና አብሮ ማሸነፍ ላይ ትኩረት ያደረገ የፖለቲካ መስመር መሆኑንም ነው አቶ መሀመድ ያስታወቁት፡፡

 

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ያለአንዳች የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ለፓርቲው አባላቶችና ለደጋፊዎቻቸው አስፈላጊው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰጠቱን የገለፁት አቶ መሀመድ ሀሰን የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን ፓርቲው በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

 

በጉባኤው በምርጫ ስነ ምግባር ፣ የአናሳ ህዝቦች መብትና አለም አቀፍ ድንጋጌዎች ላይ ፓርቲው ለእጩ ተወዳዳሪዎቹ ስልጠና የሰጠ ሲሆን የክልሉ ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴም ተመርጧል፡፡

 

የፓቲው የምርጫ ምልክት የሆነው ‹‹ብዕር›› እንዲሁም ለክልልና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩዎችም ይፋ ተደርገዋል፡፡

 

በሄኖክ ግርማ

5 8 13