የሀረሪ ጉባኤን በተመለከተ ትናንት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ምሳኔ እንደማይቀበሉት የአሚር ኑር ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የሀረሪ ጉባኤን በተመለከተ ትናንት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ምሳኔ እንደማይቀበሉት የአሚር ኑር ወረዳ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የወረዳው ነዋሪዎች የቦርዱን ውሳኔ አስመልክቶ ውይይት አካሂደዋል፡፡

 

በውይይቱ ላይ ወጣችን እና የወረዳው ነዋሪዎች ከክልሉ አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

 በውይይቱም የሀረሪ ጉባኤን በተመለከተ ሕገ መንግስቱለአናሳ ብሔረሰብ የሰጠውን መብት የኢትዮጲያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊያከብር ይገባል የሚሉ ሀሳቦች በመድረኩ ተነስቷል፡፡

 

ትናንትና ምርጫ ቦርድ የሰጠው መግለጫ ሕገ መንግስቱ የሚጻረር እና ኢ ሕገ መንግስታዊ ሂደት ነው ብለዋል፡፡ መግለጫው ከክልሉ ውጭ  ያሉትን የብሄረሰቡን ተወላጆ መብት የሚረጋግጥ በመሆኑ የሚመለከተው አካል ማስተካከያ ሊያደርግበት ይገባል ብለዋል፡፡ የተሰጠው መግለጫ ምርጫ ቦርዱን እና  ሕገ መንግስቱን የማይመጥን መሆኑን በመረዳት ሕገ መንግስቱን በማክበር ሕግን መከተል እና መስመር ይገባል ሲሉ ሀሳብ ሰተዋል፡፡ በመድረኩም የወረዳው ወጣቶች አመራሮችና እና ነዋሪዎችየምርጫ ቦርድን ውሳኔ አውግዘዋል፡፡

ነሲም መሀመድኑር

2 8 13