የሀረሪ ጉባኤ ምርጫን በተመለከተ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በመርህም በተጋባርም ፍጹም የተሳሳተ መሆኑ የሀረሪ ሙሁራን ማሕበር ገለፀ፡፡

የሀረሪ ጉባኤ ምርጫን በተመለከተ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በመርህም በተጋባርም ፍጹም የተሳሳተ መሆኑ የሀረሪ ሙሁራን ማሕበር ገለፀ፡፡

የሀረሪ ሙሁራን ማሕበር በዛሬው እለት በወቅታዊ  ጉዳዮች ዙሪያ ከሙራንና ከአባላቶቹ ጋር ምክክር አደረገ

 

የሀረሪ ሙሁራን ማሕበር 6ኘው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንደሙሁራን ማሕበርነታችን ለምርጫው ስኬታማነት እና ተአማኒነት የሚጠበቅብንን ለማድረግ ቁርጠኛበመሆን ከመንግስት ጎን እንደሚቆሚ ተናግረዋል፡፡

 

 

የሀረሪ ብሄራዊ ጉባኤን ምርጫን በሚመለከት በቅድመ ምርጫ ሂደት በምርጫ ቦርድ የተላለፈው ውሳኔ አካሄድ የክልሉን ሕገ መንግስት የጣሰ ሕገ መንግስቱንና የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፀደቀውን ደንብና መመሪያዎች የጣሰ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበረውን የምርጫ ሂደት  ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ማሕበሩ ጠይቋል፡፡

 

በተጨማሪም ማሕበሩ የኢትዮጲያ ምርጫ ቦርድ ስልጣን ሕግ ማውጣት ሳይሆን በመንግስት የወጡትን ሕግና መመሪያዎች መተግባር እንደመሆኑ መጠን ሕግ አውጪ አካል ያፀደቀውን  ሕግና ደንብ ሳይሸራረፍ በአፋጣኝ እርምት እንዲወሰድ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

 

የሙሁራን ማሕበሩ ባል አቶ አብዱናስር አብዱረህማን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የሀረሪ ሙሁራን የማሕበር የፖለቲካ ፓርቲ ነጻ የሆነ በጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን ገልጸው ወደፊት ከሕዝቡ በሰፊው የሚሰሩበት ሁኔታ እንዲ መቻች ተናግረዋል፡፡

 

ማሕበሩ በቅርብ ጊዜ እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥና የዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ለማረጋገጥ ሙሁራን የበኩላቸውን እንደሚወጡ የገለፁ ሲሆን በቅርብ ጊዜ በተለያዩ አካባቢዎች በንጹህሀን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በጽኑ እንደሚያወግዙ የማሕበሩ ተወካዮች  ተናግረዋል፡፡

 

በመድረኩ ኮቪድን የአባይ ጉዳይን፣ የኑሮ ውድነትና፣ ምርጫን በሚመለከት ምክክር ተካሂዷል፡፡

 

ዘጋቢ አሚር ኡስማን

2 8 13