የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ሰራተኞች እጅ አጠር ለሆኑ ዜጎች የምግብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ሰራተኞች እጅ አጠር ለሆኑ ዜጎች የምግብ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ሰራተኞቹ ምክር ቤቱ ባዘጋጀላቸው የኤች አይቪ ኤድስ ስልጠና ላይ የሚያገኙትን አበል አንወስድም ለእጅ አጠር ወገኖቻችን ይሁን በማለት የሰጡት ድጋፍ መሆኑን የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ  ወይዘሮ አዲስዓለም በዛብህ ተናግረዋል፡፡

 

 በዚህም  ከተለያዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ እጅ አጠር ዜጎች  የምግብ ድጋፍ መደረጉን አፈጉባኤዋ  ተናግረዋል፡፡

 

ወይዘሮ አዲስዓለም ህዝባችን ያለውን  ጥሩ የመደጋገፍ ባህል ልናጠናክር ይገባል  ሲሉም ተናግረዋል፡፡

 

ድጋፉ በብር ሲሰላ 74 ሺ ብር መሆኑንም የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ ተናግረዋል፡፡

አፈንዲ መሀመድ

8 8 13