የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ የመጀመሪያው 6 ወር አፈጻጸም ገመገመ፡፡

  የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በሁለተኛ ቀን ውሎው የሴቶች ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ  ቢሮ የ6 ወር አፈጻጸም ገምግሟል፡፡

  በቀረበው አፈጻጸም ሪፖርት ቢሮው የሴቶች ህጻትና ወጣቶች ሁለንተናዊ ደህንነት ማስጠበቅ ተሳትፎና ውክልናን ማረጋገጥ ሰፊ ስራ መሰራቱ ተገልጻል፡

  በ24 የሴክተር መስሪያ ቤቶች ላይ ያሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ ባለሞያዎች እንዲመደቡ ለህጻናት መብታቸው እንዲጠበቅ ፤ ለህጻናት ፓርላማ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱንም በሪፖርቱ ተገልጻል፡፡

  የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለበርካታ ሴቶች ተደራጅተው ስራ እንዲያገኙ የብድርና ድጋፍ መደረጉ ተገልጻል፡፡

  የሴቶች ህጻትና ወጣቶች ጉዳይ  ቢሮ መዋቅር ከማስፋት አንፃር በክልሉ በ9 ወረዳዎች ሴቶችን ህጻናት እና ወጣቶች ጉዳይ በካቢኔ ደረጃ መቋቋሙን ተገልጻል፡፡

  ሞዴል የህጻናት ማቆያ ማቋቋቋ በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሞዴል ሊባል የሚችል የህጻናት ማቆያ እያደራጀ መሆኑን  ሁሉም የክልሉ መስሪያ ቤቶችም የህጻናት ማቆያ እንዲያቋቁሙ  እየተሰራ መሆኑ ተገልጻል፡፡

  ሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ከመከላከል በኩል ከተለያዩ ግብር ስናይ ድርጅቶች፤ ከሀገር ሽግሌዎች ፤ የአፎቻና እድር አመራሮች የህክምና ባለሞዎችና ከተለያዩ ሴቶችና ወጣቶች ማህበራት ጋር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መዘጋጀቱንም ተገልጻል፡፡

  ጥቃት የደረሰባቸው 55 የሚሆኑ ሴቶች የህክምና እና የስነ ልቦና አገልግሎት እንዳያገኙ መደረጉ በሪፖርቱ ተገልፃል፡፡ጥቃት ለደረሰባቸው የማገገሚ ስፍራም መዘጋጀቱን በወጣቶች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት 499 ዪኒት ደም ግለሳ፤ አካባቢ ውበትና ፅዳት ሰፊ ስራ መስራቱን እና  1350 ወንዶችና  315 ሴት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

አገልግሎቱ በገንዘብ ሲተመን 215 ሺ እንደሚተመን በሪፖርቱ ተገልጻል፡፡

  ጉዳና ላይ የወደቀና በተለያየ ሱሶች የተጠቁ ወጣቶች  እንዲያገግሙ  ስልጠና ወስደው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እና የወጣቶች ማዕከላት እንቅስቃሴ ላይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተግዳሮት የሆነባቸው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

  በቀረበው ሪፖርት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በቋሚ ኮሚቴ አባላት ተስተዋል፡፡

 ከተነሱት ነጥቦች ባሁኑ ግዜ ሴቶች በክልሉ አመራር ውስጥ ያላቸው ሚና እና ተሳትፎ አልተብራራም፤ ለሴቶች ስራ እድል ፈጠራ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል፤ ባሁን ግዜ ከገጠር ወደ ከተማ እየመጡ ለጎዳና ህይወት እያጋለጡ ያሉ ህጻናት እየበዙ በመሆኑ  ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ፡፡

   የሀረሪ ክልል ሴቶች ህጻናት እና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ አሚና አብዱልከሪም ለጥያቀዌቹና አስተያየጦች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዘጋቢ ሀምዛ ዩሱፍ 
 25 5 13