የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡
የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀምን ገምግሟል፡፡

 በቀረበው ሪፖርት የማህራዊ ጥበቃ ስርዓት በመዘርጋት እና በማስፋፋት ዜጎችን እኩል  ተሳታፊ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ  በመንግስት ተቋማት አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እንዲፈፀሙ የተሳታፊና  የተጠቃሚነት ስርዓትን  ከመዘርጋት አንፃር በ6 ወር ውስጥ የእቅዱን 50 በመቶ  አፈፃፀም መሰራቱ ተገልጻል፡፡

   የአካል ጉዳተኛች ማህበራት እንዲጠናከሩ ድጋፍ በማድረግ መሰራቱን ፤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተጎጂ የሆኑ አካላት ድጋፍ እንዲያገኙ የተሰራ መሆኑን፤ በከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ከድህነት እንዲወጡ ለማድረግ ዘለቂ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 1085 ተጠቃሚዎች በየወሩ 315 ብር በ6 ወሩ መከፈሉ እና ይህንንም በቅርበት  በመከታተል ለሚመለከተው አካል ግብረ መልስ ለመስጠት መቻሉም ተገልጻል፡፡

ባጠቃላይ ብር 2 ሚሊዮን 50 ሺ 650 ብር መከፋፈሉ እና  በገጠር ሴፍቲኔት ዘላቂ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን በተመለከተ ለ2056 ሰዎች በየወሩ 275 ብር መከፋፈሉና  በ6 ወሩ ጠቅላላ 5 ሚሊየን 443 ሺ 50 ብር መከፈሉን በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

በአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ በድርጅቶች መሰረታዊ ስራ ሁኔታ ቁጥጥር ማሳደግና ማስፋፋትን በተመለከተ  150 ክትትል ለማድረግ ታቅዶ በ6 ወር 65 መከናወኑንና የእቅዱን  43 በመቶ  አፈፃፀም መመዝገቡ እንዲሁም  የአረጋውያ ድጋፍ በተመለከተ በአብርሃ ባህታ አረጋውያን ማቆያ ውስጥ የተለያዩ የማደራጀት ስራዎች መሰራታቸውን እና ጎዳና ላይ የወደቁትን ወደ ማእከሉ ማስገባትና በማእከሉ  በተለያዩ ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባሻገር ማህበራዊ የምክክር ስርዓቶችን ማጎልበት ላይ፤ ለህጻናት ማሳደጊያዎች የማጠናከሪያ የአቅም ግንባታዎችን ተደራሽ ማድረግ ላይ ፤ማህበራትና ድርጅቶች እንዲጠናከሩ የምክር ድጋፍ ማድረግና የስራ ስምሪት አገልግሎት ለማስፋፋትም  አሰራሮችን ወቅቱ በሚፈቅደው መሰረት የማሻሻል እና ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል የማድረግ ስራ መሰራቱንም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

የአሰሪና  ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይም አስፈላጊውን ክትትል እና ቁጥጥር የማድረግና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር መከላከል ላይም ከአጎራባች  ክልሎች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑም ተገልጻል፡፡

በሪፖርቱ ላይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄና አስተያየት አንስተዋል፡፡

ከተነሱት ነጥቦች መካከልም በአቅመ ደካሞች ድጋፍ ዙርያ የተሰራው ስራ ጥሩ መሆኑን እንዲሁም በአብርሃ ባህታ የአረጋውያን ማቆያ አካባቢ ያለው ጉምሩክ ሊነሳና ወደ ሌላ ቦታ ሊዘዋወር ይገባል፤ ከሌሎች አካላት ጋር ቅንጅታዊ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል የጎዳና ህይወትን የሚመሩትን ማንሳት  ብቻ ሳይሆን አዳዲስ ልጆች ወደ ጎዳና እንዳይወጡ መሰራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በተሰጡት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ዙርያ የሰራተኞችና ማህበራዊ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ምስራቅ እሸቴ ምላሽ እና  ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዘጋቢ ሀምዛ ዩሱፍ 
28 5 13