የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉ የልዕቀት ማእከል የ6 ወር አፈጻጸምን ገመገመ፡፡

የሐረሪ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ የክልሉ የልዕቀት ማእከል የ6 ወር አፈጻጸምን ገመገመ፡፡

የልህቀት ማእከል ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት ማዕከሉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስራ አቋርጦ የነበረ መሆኑን ተገልጻል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት ትምህርት እንዲጀመር ከተወሰነ በኋላ የማዕከሉን የምዘና አገልግሎት ለማስጀመር  ዝግጅት ሲደረግ  ነበር በማለት ተገልጻል፡፡

ከዝግጅቶች መካከል ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ በተሰጠ አቅጣጫ ማኑዋል ተዘጋጅቶ አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተለያዩ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ከኮሮና በኋላ እንዴት ሊሰሩ እንዳቀዱ ምልከታ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ከጥቅምት ወር ጀምሮ ለ1165 ተማሪዎችና ለባለሞያዎች የብቃት መመዘኛ  የምስክር ወረቀትም የተሰጠ መሆኑን ተገልጻል፡፡

የተለያየ አሰራር ማሻሻያዎች እየተከናወኑ መሆኑ  በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ አያያዝ በመዘርጋት እየሰሩ መሆኑ  ከፌደራል እና ከድሬደዋ ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ የመጡ ልዑካን ቡድኖች የማዕከሉ  ስራ ከመረጃ አያያዝ ማዘመን ጋር ተያይዞ ተሞክሮ መውሰዳቸውን የመመዘን አቅማቸው በቀን ከ5-9 ሰዎች ማሳደግ መቻሉን ተገልጻል፡፡

የማዕከሉ አቅም ለማሳደግም የተለያዩ የልምድ ልውውጥ ስራዎች መሰራታቸውን በሪፖርቱ ተገልጻል፡፡

ከባለፈው አመት አጋማሽ ጀምሮ ተከስቶ የነበረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የፋይናንስ አፈፃፀማቸው ላይ ተፅዕኖ እንደነበረው ተገልፃል፡፡

የህዝብ ግንኙነት ስራ በተመለከተ ከሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሲ ጋር በመሆን በምዘና ዙርያ  በ3 ቋንቋ የተለያዩ መረጃዎች የማስተላለፍ ስራ መካሄዱ  ተገልጻል፡፡

እንዲሁም በፌስቡክ ገጽ በስፋት መረጃ ማስተላለፍ መቻሉን ተነስቷል፡፡

ከሙስና እና ኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ተያይዞ ለሰራተኞች ስልጠናዎች መስጠቱንና እምነት ያጎደሉ ላይ እርምጃ መውሰዱን በሪፖርቱ ተገልጻል፡፡

በቀረበው ሪፖርት የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጥያቄና አስተያየት አንስተዋል፡፡

ከተነሱት ነጥቦች መካከል  ማእከሉ ለኪራይ ሰብሳቢነት ተጋላጭ ከሆኑ ተቋማት አንዱ ስለሆነ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በቴክኖሎጂ የተደገፉ የመረጃ አያያዝ ተግባራዊ ማድረጋቸው ተጠናክሮ ይቀጥል የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
የሐረሪ ክልል ልህቀት ማእከል ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱላዚዝ አደም ለተነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዘጋቢ ሀምዛ ዩሱፍ 
26 5 13