የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የካቢኔ አባላት በባለሀብቶች እየተገነቡ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የካቢኔ አባላት በባለሀብቶች እየተገነቡ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡

በሀረር ከተማ በተለምዶ ሀማሬሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መንደር በተካሄደው  ጉብኝት በመንደሩ የተለያዩ የኢንደስትሪ ውጤቶችን ያመርታሉ የተባሉ የተለያዩ በግንባታ ላይ የሚገኙ ሼዶች አሁናዊ ሁኔታ ምልከታ ተደርጎበታል፡፡

 

በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ማምረቱ ይገባሉ ከተባሉ አምራች እንደስትሪዎች መካከል የፕላስቲክና ከረጢት፣የኦክሲጅን እንዲሁም የቆርቆሮና ሚስማር ማምረቻዎች እንዲሚገኙበት ተነግሯል፡፡

 

በአግልግሎቱ ዘርፍም የሐረሪና የኦሮሞ ባህላዊ እሴትን የያዘ ግዙፍ ሎጅ የግንባታ ሂደትም በልኡክ ቡድኑ ተጎብኝቷል፡፡

 

ክልሉን ወደ ኢንደስትሪ ማዕከልነት ለማሻጋገር እየተከወኑ ያሉ ሥራዎች ምን እንደሚመስሉ ጉብኝት በተደረገበት መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ  የግንባታ ሒደታቸው በአንጻራዊነት በመልካም ጎኑ የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸው ከሀገራዊ ብሎም ከክልላዊ ፍላጎት አንጻር በፍጥነት የግንባታ ሂደታቸው ተጠናቆ ወደ ማምረቱ እንዲገቡ ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ባለሀብቶቹ በግንባታም ሆነ በማምረት ሂደታቸው የሚገጥማቸው ችግር ካለ በህጋዊ መንገድ በማቅረብ የክልሉ መንግስት ውሳኔ የሚሰጥበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው ወደ ሥራ ሲገቡ ለበርካታ የሥራ አጥ ዜጎች ጊዜያዊና ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

ወንድሙ አዱኛ

28 7 13