የሐረሪ ክልል ግብርና ቢሮ ከ22 ሺ በላይ ነዋሪዎች በሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ እያደረገ እደሚገኝ ገለፁ፡፡

የሐረሪ ክልል ግብርና ቢሮ ከ22 ሺ በላይ ነዋሪዎች በሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ እያደረገ እደሚገኝ ገለፁ፡፡

በክልሉ የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ነዋሪዎች በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና እንክብካቤ እየተሳተፉ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በክልሉ እጅ አጠር የሆኑ ዜጎችን  በተለያዩ መስኮች ተጠቃሚ ሲያደርግ የቆየው ሴፍትኔት ፕሮግራም በአሁኑ ወቅትም ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

 

የአሁኑን ፕሮግራም ከዚህ በፊቱ ለየት የሚያደርገው የገጠሩን የማህበረሰብ ክፍልንም  በተፈጥሮ ሀብት ልማት ጥበቃ እንዲሳተፉ በማድረግ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ በሀረሪ ክልል ግብርና ልማት ቢሮ የሴፍትኔት ፕሮግራም ሀላፊ አቶ አብዲ ኡመር ተናግረዋል፡፡

 

በዚህ ፕሮግራም በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ዘርፍ  የገጠሩ ህብረተሰብም በተፋሰስ ልማት ስራ  እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

 

በዚህ ረገድ በተሰራው ስራም ከዚህ በፊት ገላጣና በአፈር መሸርሸር ምክንያ እጅግ የተጎዱ ተራሮች በአሁኑ ወቅት ወደ ለምለምነት እየተመለሱ እንደሚገኙና በተከናወኑት የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ወደ ቀድሞ ይዞታ በመመለስ ላይ መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ፡፡

 

ነዋሪዎቹ እንደሚሉት በአሁኑ ወቅት በገጠሩ ወረዳዎች እየተሰሩ በሚገኙ ስራዎች አፈር እንዲንሸራሸር የሚያደርጉ የተለያ ምክንያቶች ላይ በመስራታችን  ከዚህ በፊት የደረቁ ምንጮች ተመልሰው እየጎለበቱ ይገኛል ይላሉ፡፡

 

በዚህ አገልግሎት ህብረተሰቡ አካባቢውን እየተንከባከበ ራሱንም ተጠቃሚ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑንና ህዝቡ በሀላፊነት መንፈስ ለስራው ከፍተኛ ተነሳሽነት እያሳየ መሆኑንም ነው የገለፁት፡፡

 

በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ከሆነው 22 ሺ በላይ ሰዎች  ውስጥ 52 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን አቶ አብዲ ተናግረዋል፡፡

 

ዘጋቢ ምስክር አለማየሁ

11 8 13