የሐረርን የሰላም የፍቅር እና የመቻቻል እሴት ለማስመለስ እንደሚሰራ የሀኪም ወረዳ አስታወቀ፡

የሐረርን  የሰላም የፍቅር እና የመቻቻል እሴት ለማስመለስ እንደሚሰራ የሀኪም ወረዳ አስታወቀ፡

 

ላለፉት 2 ዓመታት በሀረሪ ክልል ካሉ እና ከፍተኛ የስጋት ቀጠና ውስጥ ከሚመደቡ ስፍራዎች መካከል የሀኪም ወረዳ ግንባር ቀደም ስፍራ የሚይዝ ነበር ፡፡

 

ቀደም ሲል በወረዳው የተደረገ የአመራር ሽግሽግን ተከትሎ በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡

 

ለውጡ ደግሞ በቅርብ በተካሄደው የክልሉ ካቢኔዎች እና ወረዳዎች የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተመስክሯል፡፡

 

የሀኪም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቶውፊቅ መሀመድ ሐረር የምትታወቅበትን የሰላም እና የመቻቻል እሴት ለማጎልበት የወረዳው የሰላም አምባሳደሮች ለነዋሪዎቹ የሰላም ጥሪ ለማድረግ የተካሄደ የሰላም ጉዞ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኮማንደር ናስር ከድር የወረዳው ህብረተሰብ ሰላሙን ለመጠበቅ ከፀጥታ አካላቱ ጋር እያደረገ ላለው  ቅንጅት አመስግነዋል፡፡

 

ሀኪም ወረዳ በርካታ የፀጥታ ችግር ሲስተዋልበት የነበረ እና የስጋት ቀጠና እንደነበር የገለፁት ደግሞ የወረዳው የሰላም እና ፀጥታ ሀላፊ አቶ ያህያ አብዱሰላም ናቸው፡፡

 

ሀላፊው በወረዳው ያሉ ቀበሌዎች እና ሰፈሮች ውስጥ የሰላም ቤተሰቦች እና አምባሳደሮች እንዲሁም ገለልተኛ አማካሪ ቡድን አደራጅቶ ለሰላም እና ለልማት ዘብ እየቆሙ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

 

በሰላም ጉዞ ላይ የተሳተፉ የሐገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች ከሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ኤጀንሴ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሰላም እንዲረጋገጥ ህብረተሰቡ ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለበት ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

 

የአካባቢያቸውን ሰላም እና ፀጥታ ይበልጥ ለማስጠበቅ እንደሚተጉም ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ፋህሚ ዚያድ