የሐረር ታሪክ ለትውልድ ማሳለፍ ሁላችንም ሀላፊነት አለብን ፡፡

0
215

የሐረር ታሪክ ለትውልድ ማሳለፍ ሁላችንም ሀላፊነት አለብን በማለት የሐረር ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ሹክሪያ አህመድ ገለጹ፡፡
ከንቲባው ይህ የተናገሩት በትናንትናው እለት የታሪክ ምሽት በተከበረበት ወቅት ነው፡፡
የታሪክ ምሽቱ ባህላችን ቋቋችንና ታሪካችንን ለመጪው ትልውድ እናስተላፋን በሚል መሪ ቃል በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረው፡፡
በመድረኩ ሐረር በ1010 ዓመቷ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዋን የሚያሳይ ጹሁፍ በመድረኩ ቀርቧል፡፡
ሐረር 1010 አመታት ውስጥ 72 የሚሆኑ አሚሮች ተፈራርቀው እንደነገሱበትና ሁሉም አሚሮች ለሐገራቸው በጎ ተግባራትን ማበርከታቸው በቀረበው ጹሁፍ ተዳሷል፡፡
የሴቶች መብት ከድሮውም ጀምሮ መከበሩ እና የመሬት ባለሀብትነታቸው መጠበቁ ከተማዋ ከጥንት ጀምሮ በፖለቲካው ዘርፍ ያላትን ስልጣኔ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ተብሏል፡፡
ሀረር በግብርና ምርት ስትተዳደር መቆየቷና በዋነኛነትም በቡና ምርት ትታወቅ እንደነበረም ተገልፃል፡፡
ከቻይና ሐገር የመጡ ተመራማሪዎች ባደረጉት ምርምር 200 ዓመት በላይ እድሜ ያለው የቡና ተክል መኖሩ መረጋገጡም ለዚህ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው ተብሏል፡፡
በጦርነት ሳቢያና በወረራ ምክንያት መሬታቸውን ማጣታቸውን የግብርናውን ዘርፍ በመተው ፊታቸው ወደ ንግድ እንዲያዞሩ ተገደዋል፡፡
በንግዱ ዘርፍም ቢሆን ሀረሪዎች ውጤታማ ሆነው መቀጠል መቻላቸው ነው በጽሁፉ የተብራራው፡፡
ወደ የመን፣ ህንድ እንዲሁም አውሮፓ ሀገራት ምርታቸውን የሚልኩበት ጊዜም እንደነበርም በጽሁፉ ተመልክቷል፡፡
የሐረር ታሪክና ባህል ከእስልምና እምነት ጋር ጥልቅ የሆነ ቁርኝት እንዳለው ነው በመድረኩ የተገለፀው፡፡
አዋቾች የሀይማኖት ስፍራ ከመሆናቸውም ባሻገር የተጣሉትን ለማስታረቅ ጥቅም ይሰጡ ነበር ተብሏል፡፡ በቀረበው የሀረር ታሪክ ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በመድረኩ ለተነሱት ጥያቄዎች የታሪክ ባለሙያዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰተዋል፡፡
ዘጋቢ ነሲም መሀመድ
5/11/09

NO COMMENTS