የምርምር ውጤቶች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ሀገሪቱ ለምታወጣው ፖሊሲ ለመነሻነት ሊያገለግሉ ይገባል አለ የሀረማያ ዪኒቨርሲቲ፡፡

የምርምር ውጤቶች ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ሀገሪቱ ለምታወጣው ፖሊሲ ለመነሻነት ሊያገለግሉ ይገባል አለ የሀረማያ ዪኒቨርሲቲ፡፡

የሀረማያ ዩኒቨርሲሰቲ 37ኛ እና የ38ኛውን የምርምር ስርጸት የማሕበረሰብ ተሳትፎ ጉባኤ አካኒዷል፡፡

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከተመሠተረበት ወቅት አንስቶ ለሀገሪቱ የተማረ ሰው ሐይል ፍላጎት ለማሟላት  አስተዋጽኦ ካደረጉ አንጋፋ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ይጠቀሳል፡፡

 

ዩኒቨርሲቲው የአፍሪካ የምርምር ልህቀት ማዕከል ለማድረግ ከሚሰራው ሥራ ውስጥ ደግሞ ችግር ፈቺ የምርምር ሥራ ተጠቃሽ ነው፡፡

 

ዩኒቨርሲቲው የሚሰራውን የምርምር ስራ ደግሞ በየአመቱ በመገምገም ደካማና ጠንካራ ጎኖችን የሚለይበትን ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

 

የዚህ አመታዊ ጉባኤ አካል የሆነው 38ኛው የምርምር ስርጸት የማሕረሰብ ተሳትፎ ጉባኤ ላይ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶክተር ተስፋዬ ለማ እንዳሉት በሀገራችን የሚደረጉ የምርምር ሥራዎች በተጨባጭ የሕበረተሰብ ችግርን በመፍታት በኩል የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች አንጻር የተሻለ ልምድ አለው ብለዋል፡፡

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ሥራዎችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም በዘርፉ የሚሰሩ ምሁራንን በማበረታታት በቀጣይ በትኩረት ከሚከናወኑ መስኮች መካከል ነውም ብለዋል፡፡

 

የምርምር ውጤቶች በተጨባጭ ማሕበረሰቡን የመለወጥ ግብ ያላቸው ሥራዎች ሊሆኑ ይባል ያሉት ደግሞ የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ፕ/ር መንግስቱ ኡርጌ ናቸው፡፡

 

ፕ/ር መንግስቱ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዘርፎችን ማስፋት ብቻ ሳይሆን ጥልቀትና ምጥቀት ላይ ትኩረት በማድረግ ዘርፈ ብዙ ክንውን እየሰጠ መሆኑን አብራርተው በዚህም ከ300 በላይ የምርምር ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ዘርፍ ያለውን የካበተ  ልምድ ለሐገር እድገት አስተዋጽኦ ለማድረግ የተሰሩ መስኮች  ከግዜ ወደ ግዜ  እየሰፉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር መንግስቱ እንዳሉት የተሰሩ ምርምሮችን መገምገምና ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ለቀጣይ ስራ ግብአት እንዲሆኑ ታሳቢ ያደረገ ጉባኤ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

 

በተለይም የሐረማያ ዩኒቨርሲሰቲ በግብርናው ዘርፍ ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ በቀጣይም ይህን ልምድ ማስፋት ተጠቃሚዎችንም ይበልጥ ከፍ ለማድረግ የሚከናወኑ ሥራዎች በርካታ ናቸው ብለዋል፡፡

 

 

ፕሮፌሰር መንግስቱ ኡርጌ እንዳሉት ለማሕበረሰብ ጥቅም ላይ ትኩረት ያደረገ ሥራ በመሥራት እንደ ሀገር የተጀመሩ የልማት እቅዶችን ለማሳካት ብሎም ድህነትን ለመቀነስ የላቀ ቦታ አለው ብለዋል፡፡ ጉባኤው የኮሮና ቫይረስ በአሀገር ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ስጋት በሆነበት ወቅት ስርጭቱን ለመግታት የሚደረጉ የመከላከል ስራዎችንም ጎን ለጎን በመከወን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

ተማራማሪዎችም በምርምሩ ዘርፍ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን እየተቋቋሙ ውጤታማ ስራ እያከናወኑ ሲሆን ዩኒቨርሲቲውም ተግዳሮቶቹን ለማለፍ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በተቻለው ሁሉ በሟሟላት ያግዛል ብለዋል፡፡

 

በምርምር ረገድ ያለውን ሙሉ አቅም በመጠቀም በተለያዩ መስኮች የተለያዩ የምርምር ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ደግሞ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ጉዳዮች ፕሬዝዳንት ዶክተር ተስፋዮ ለማ ናቸው፡፡

 

የምርምር ሥራዎቹ በርካታ ውጤቶችን እያስገኙ ነው ያሉት ዶክተር ተስፋዬ ለጤና ፖሊሲ ግብአት የሚሆኑና የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚያገለግሉ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ የሚያግዙም ጭምር ይገኙበታል ብለዋል፡፡

 

ባለፉት ዘመናት የምርምር ሥራ ተብሎ የሚመደብ በጀት እንዳነበረ ያወሱት ዶክተር ተስፋዬ ለማ ዛሬ ግን በመንግስት በኩል ከ54 ሚሊየን ብር በላይ እና ከድጋፍ አድራጊዎች ጋር በሚሰሩ   ቅንጅታዊ ሥራዎች ከ70 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት 75 የምርምር መስኮች ላይ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

 

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየሰራቸው ካሉት የምርምር ሥራዎች መካከል በቀዳሚነት በግብርናው ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ ሲሆን በጤናው ዘርፍ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ምርምር የተሻለ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ምስጋናው ሐይሉ

1 8 13