የሴት ልጅ ግርዛትን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት መላው ህብረተሰብ በባለቤትት ሊሰራ እንደሚገባ ያነጋገርናቸው ሴቶች ገለፁ፡፡

የሴት ልጅ ግርዛትን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት መላው ህብረተሰብ በባለቤትት ሊሰራ እንደሚገባ ያነጋገርናቸው ሴቶች ገለፁ፡፡

ግርዛት በሴቶች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት በተለያየ መገናኛ ብዙሀን ይነገራል፡፡

በተለይ ግርዛት በወሊድ ግዜ በሴቶች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ቀላል እንዳልሆነ የህክምና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

ግርዛት በሴቶች ላይ የሚያደርሰውን ጉዳትና የሴቶች ጥቃት ለማስቀረት በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የሴቶች ፀረ ግርዛት ቀንን ብቻ መጠበቅ የለብንም የሚሉት ያነጋገርናቸው ሴቶች ሀሳባቸውን  ለሀረሪ ብዙሀን መገናኛ ሰተዋል፡፡

በሴቶች ላይ በግርዛት ምክንያት የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት ማህረሰቡን ያሳተፈ ስራ መካሄድ እንዳለበት አስተያት ሰጪዎቹ ገልጸዋል፡፡

  ግርዛት በሴቶች ላይ የሚያደርሰውን ጉደት ለማስቀረት በገጠር ማህበረሰብ ላይ ሊሰራ እንደሚገባ እና  በድብቅ ግርዛን የሚፈፅሙ ሰዎችን ወደ ህግ ማቅረብ አለብን ሊሱ ነው የተናገሩት፡፡

ግርዛት በሴቶች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ላይ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መስጠት እንደሚገባም ሴቶች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በሴቶች ላይ በፆታ ስነ ልቦና በማህበራዊ በኩል ግርዛት የሚያደርሰው ጉዳትን የሀይማት አባቶች አባገዳዎች የሀገር ሽማግሌዎች ሁሉ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አለም አቀፍ የሴቶች የፀረ ግርዛት ቀን ጥር 28 በአለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል፡፡

ዘጋቢ አለም ገመቹ 
26 5 13