የሴክተር ቢሮዎች ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ የመቀንጨር በሽታን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ፡፡

የሴክተር ቢሮዎች ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ የመቀንጨር በሽታን ለመከላከል ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገለፀ፡፡

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሀረሪ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንደተናገሩት ሀገሪቱ ፈጣን ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ዕድገት ለማምጣትና ዘላቂ የልማት አቅም ለመገንባት ለዜጎች የምግብ አቅርቦትና ተደራሽ ነት ማረጋገጥና ጥራቱን ፣ ደህንነቱና የንጥረ ምግብ ይዘቱ የተሟላ ምግብ የሚመገብ ጤናማ ፣ አምራችና የፈጠራ ብቃት ያለው ዜጋ መገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

 

የምግብና የስርዓተ ምግብ ትግበራ ስራ በክልሉ ከተጀመረ ጥቂት ጊዜያት እንዳስቆጠረ የገለፁት ምክትል ርዕስ መስተዳድሯ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ስራዎች በባለቤትነት በቂ ትኩረት ተሰጥቶ ሲከናወን እንዳልነበረ ገልጸዋል፡፡

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመቀንጨር በሽታን ለመቀነስ የታቀዱትን ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ ላይ የሚመለከታቸው ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠትና ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

 

በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የምግብ አለመመጣጠን ችግር /የመቀንጨር በሽታ / የምግብና ስርዓተ ምግብ ፖሊሲ፣ የሀገራችንንና የክልሉን ነባራዊ ሁኔታን የሚያሳይና ከምክር ቤት አባላትና ለሴክተር መስሪያ ቤቶች ምን ይጠበቃል በሚል ርዕሶች ላይ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

 

ውይይቱን የመሩት የሀረሪ ክልልምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አዲስ አለም በዛብህ እንደተናገሩት የምግብ ሰርዓተ ምግብ ፖሊሲውን ለማስፈጸም የምክር ቤት አባላቶች የበኩላቸውን መውጣት እንዳባቸው ገልጸው በማሕበራዊና በኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ችግር የሚፈጠረው የመንቀጭር በሽታ ለማጥፋት ግንዛቤ በፍመጠርና ቅንጅታዊ አስራርሮችን በማጠናከር መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

 

  በሀገራችን ለውጥና ዕድገት ለማምጣት በወረቀትም ከተቀመጠው ባሻገር ሁሉም አመራር በተግባር  ለውጥ ሊያሳይበት እንደሚገባ አሳስበው ቅንጅታዊ ስራዎች መስራታቸውም ትልቅ ጉልበት ሊሆኑ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

 

በመድረኩ ላይ ጽሑፍ ያቀረቡት የክልሉ ርዕስ መስተዳድር  የምግብና ስርዓተ ምግብ አማካሪ አቶ አብዱናስ አህመድ በበኩላቸው የክልሉ ከፍተኛ አካላት የክልሉ ቱክኒካል ኮሚቴዎች በሚሰሩት የምግብና ስርዓተ ምግብ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማዳበር የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ለማስቻል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

 

በትዕንት ደባልቄ

6 8 13