የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 20ኛ አመት ምስረታ በማስመልከት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙ ለ9ኛ እና ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ተሰጠ፡፡

የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 20ኛ አመት ምስረታ በማስመልከት በወረዳ ደረጃ ለሚገኙ ለ9ኛ እና ለ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተና ተሰጠ፡፡

  የኮሚሽኑን 20ኛ አመት የምስረታ በዓልን በማስመልከት ሚያዝያ 1 በትምህርት ቤቶች ደረጃ ለ9ኛ እና 11ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያየ የግልና የመንግስት ኮሌጅ ተማሪዎች ከዩንቨርስቲዎች በተወጣጡ ተማሪዎች መካከል ውድድር መካሄዱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

 

 ፈተናው እየተሰጠ ያለው በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲሆን በትምህርት ቤቶች ደረጃ የተካሄደው ውድድር ላይ አብላጫ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዛሬ በወረዳ ደረጃ በተካሄደው ፈተና ላይ ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል፡፡

 

በዘህ መሰረትም በወረዳ ደረጃ የሚሰጠው ፈተና በሀረሪ ክልል ተካሄዷል፡፡

 

በወረዳ ደረጃ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች ሚያዝያ 19 በክልል ደረጃ ይፈተናሉ፡፡

 

በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ግንቦት 16 የሁሉም ክልል አሸናፊዎች እንደሚፈተኑ ከሀረሪ ክልል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

አለም ገመቹ

7 8 13