የብርሃን ምዘና በሀረሪ ክልል እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

የብርሃን ምዘና በሀረሪ ክልል እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ፡፡

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የተማሪዎች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሁሴን እንደተናገሩት የዘንድሮው የጎልማሶች ትምህርት የብርሃን ምዘና በክልሉ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

 

1200 ጎልማሶችን ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ  ከ1600 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች በክልሉ 9 ወረዳዎች  የብርሃን ምዘና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

 

በትምህርት ደረጃ መሰረታዊ ግንዛቤ ያለው ህብረተሰብ ለማፍራትም እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡

 

የተማረ የህብረተሰብ ክፍል በኢኮኖሚ በማህበራዊ በፖለቲካዊም ትልቅ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

 

እንደ ሀገር  የጎልማሶች ትምህርት የብርሃን ምዘና ለመጀመሪያ ግዜ እየተሰጠ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

 

በክልሉ ትምህርት ቢሮ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ቡድን መሪ አቶ አቅናው መኩሪያ  በበኩላቸው የዘንድሮው የጎልማሶች የትምህርት ምዘና በሁሉም ክልሎች እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

 

አለማውም በጎልማሶች ትምህርት የብርሃን ምዘና የሚወስዱ ዜጎች  በቀጥታ ከ3ተኛ ክፍል የተማሪ አቅም ጋር አቻ የሚያደርግ እውቅና መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

 

40 ሺ ከሚሆኑ  የክልሉ ጎልማሶች ውስጥ 20 ሺው ወደማንበብና መፃፍ መሸጋገሩን ተናግረዋል፡፡

 

የጎልማሶች ትምህርት የብህራን ምዘና እየወሰዱ የሚገኑ ጎልማሶች በበኩላቸው ከትምህርቱና ምዘናው  ትልቅ ጥቅም ያገኙ መሆኑን  ገልፀዋል፡፡

 

በህይወት የእለት እንቅስቃሴም በተሻለ ደረጃ ነገሮችን መመዘን የሚያስችል አቅም ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

 

ዘጋቢ አሚር ኡስማን

                                                    

22 7 13